Home / ፖለቲካ / ሱሌማን አብደላ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አረጋገጠ

ሱሌማን አብደላ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አረጋገጠ

የማኅበረሰብ አንቂው ሱሌማን አብደላ ከሳውዲ አረቢያ በግዳጅ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላለፎ መሰጠቱን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ከአንድ ዓመት ከግማሽ በላይ ለሚሆን ጊዜ ከሚኖርበት ሳውዲ አረቢያ ደብዛው የጠፋው ሰሌማን ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፎ መሰጠቱን በሪፖርቱ ተገልጿ፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሱሌማንን ተላልፎ መሰጠት ያረጋገጠው ይፋ ባደረገው የፈረንጆቹ 2024 የነበረውን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ የሚዳስስ ሪፖርት ላይ ነው፡፡

ቀደም ሲል በታላቁ የህዳሴ ግድብ በአረብኛ ቋንቋ ተሟጓችነቱ የሚታወቀው ሰሌማን አብደላ በሳውዲ አረቢያ የታሰረው በአማራ ክልሉ የመንግሥት እና የፋኖ ኃይሎች መካከል ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ነው፡፡

ሱሌማን በወቅቱ የፋኖ ኃይሎችን እንቅስቃሴ በመደገፍ በመንግሥት ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲያስተባብር ነበር የሚሉ ምክንያቶች ለመታሰሩ እንደምክንያት ሲጠቀስ እንደነበር በርካታ መረጃዎች መውጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡ በዚሁ የፖለቲካ አቋሙ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሳውዲ አረቢያ መንግሥት ባቀረበው ጥያቄ ከታሰረ በኋላ ወደ አዲስ አበባ መወሰዱ ተያይዞ ሲገለጽ ነበር፡፡ በሳኡዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሱሌማንን በሚመለከትና ያለበትን ሁኔታም ለማረጋገጥ በርካታ ሙከራዎችንም ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሰበት ሪፖርቱን ይፋ ቢያደርግም ሪፖርቱ ሱሌማን በሁለትዮሽ የአገራት ግንኙነት ጫና ተላልፎ ከመሰጠቱ የዘለለ ዝርዝር መረጃ አላጋራም፡፡

የማኅበረሰብ እንቂው በድንገት ከጠፋ በኋላ በሳውዲ አረቢያ መንግሥት መታሰሩ ሲገለጽ ነበር፡፡ ሱሌማን በሚኖርበት ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያ መንግሥት ጥያቄ ከታሰረ ከሁለት ወራት ገደማ በኋላ ተላልፎ መሰጠቱ ታውቋል፡፡

ሱሌማን ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ ስላለበት ሁኔታ በውል የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ሱሌማን ከሚኖርበት ሳውዲ አረቢያ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፎ ከተሰጠ የት እንዳለ አይታወቅም፡፡

ሱሌማን ታስሮ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፎ እንዲሰጥ በማድረግ የወቅቱ የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ጣት የሚቀሰርባቸው ቢሆንም አምባሳደሩ የቆይታ ጊዜያቸውን አጠናቀው ከሪያድ በተሰናበቱበት ወቅት ሱሌማንን እንዳላሳሰሩ ማስተባበያ ሰጥተዋል፡፡

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *