ባለፉት ጥቂት ቀናት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን በወርቅ ማውጣት ሥራ ላይ በተሰማሩ ወጣቶች እና በአካባቢው አስተዳደር መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ሰንብቷል። ይህንኑ ተከትሎ በተከሰተ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱና በመጨረሻም ጉዳዩ በውይይት መፈታቱ ታውቋል። ለግጭቱ መነሻ የሆነው የዞኑ አስተዳደር በቃፍታ ሑመ...
በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የታጠቁ ኃይሎች የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ ለመዝረፍ ያደረጉት ሙከራ፤ ጥሬ ገንዘብ አስቀድሞ በመሸሹ ሙከራው ሳይሳካ መቅረቱን ምንጮች ለሆርን ፍሪኩዌንሲ ገለፁ በከተማው ውስጥ የሕወሃት ታጣቂዎች ናቸው የተባሉ የታጠቁ ኃይሎች በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ ቅርንጫፎችን ...
ለተከታታይ ስምንት ዓመታት የተለያዩ መረጃዎችን ለሕዝብ በማድረስ ሰፊ ተደራሽነት የነበረውና በቅርቡ ከሳታላይት የወረደው አሻም ቲቪ ሙሉ በሙሉ የተዘጋው መንግሥት ባቀረበበት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የግብር ጫና መሆኑን ምንጮች ለሆርን ፍሪኩዌንሲ አስታውቀዋል። ጣቢያው በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮና በፌደራል ገቢዎች ሚኒ...
መንግሥት በነዳጅ ምርቶች ላይ የጣለው የ30 በመቶ እሴትና ኤክሳይዝ ታክስ ከመጪው ታህሳስ ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ፣ ማደያዎች ከጭማሪው ለማትረፍ ነዳጅ እየደበቁ እንደሆነ እና ይህንንም ተከትሎ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በነዳጅ ዋጋ ላይ መታየቱን ሆርን ፍሪኩዌንሲ አረጋግጧል፡፡ የነዳጅ ማደያዎች ከወዲሁ...
በድንበር አካባቢ የኤርትራ ገንዘብ ናቅፋ ግልጋሎት ላይ እየዋለ ነው የጥሬ ገንዘብ እጥረቱ በተለይም በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር አቅራቢ በሚገኙ ከተሞች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነው ተብሏል። እንደ አዲግራት፣ አክሱም፣ አድዋና ሽሬ ባሉ ከተሞች ባንኮች ለደንበኞቻቸው የሚሰጡት ጥሬ ገንዘብ ውስን መሆኑን እና ተጠቃሚዎ...
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮሪደር ልማት የተሰሩ የንግድ ቤቶች ኪራይ ጨረታን ለማሸነፍ በሚልዮኖች ብር ጉቦ እየተጠየቀበት መሆኑን ለዝግጅት ክፍላችን የደረሱት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በመዲናዋ በተለያዩ አደባባዮችና መንገድ ዳር በኮሪደር ልማት የተገነቡ የመንግሥት የንግድ ቤቶች በሁለት ዙር ለጨረታ ቀርበው ነበር። ...
በተቀናጀ መንገድ ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሬ አሻጥር ላይ ተሰማርተዋል ያላቸው 112 ተጠርጣሪዎች፣ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልገሎት አስታውቋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል ሰባት የውጭ አገራት ዜጎች እንደሚገኙበት አገልግሎቱ ያሰረጫው መረጃ ያመላክታል። ሕገ- ወጥ ሃዋላዎች ፣ የ...
የአንድ ወር ጭማሪ 9 ቢሊዮን ብር ነው መንግሥት ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ያለው የደመወዝ መዘግየት፣ በሰራተኛው ዘንድ ቅሬታ መፍጠሩን ተከትሎ በገንዘብ ሚኒስቴር ትዕዛዝ በአስቸኳይ ክፍያ እየተፈጸመ መሆኑን ረተድተናል። ከመስከረም 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው የደመወዝ ጭማ...
መንግስት የተደረገ ጭማሪ የለም ብሏል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚተዳደሩት የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት እና ሌሎች ፐብሊክ ባሶች የትራንስፖርት ክፍያ ታሪፍን በድንገት በእጥፍ በማሳደጋቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣና ሮሮ አስነስቷል። በደረሰን መረጃ መሰረት፤ የሕዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰ...
የጣና ሐይቅ ላይ የቱሪዝም እና የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ በርካታ ወጪ እና ወደ መሃል አገር የማጓጓዝ ስራ የተሰራባት “ጣናነሽ ቁጥር ፪” ጀልባ በአሁኑ ሰዓት በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እጀባ ካልተደረገላት ሙሉ አገልግሎት እንደማትሰጥ ተገለጸ። የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ...









