Home / ፖለቲካ / በቡታጅራ ከተማ በተፈጠረ ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ተጎዱ

በቡታጅራ ከተማ በተፈጠረ ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ተጎዱ

በወልቂጤ በፖሊስ ጣቢያ በደረሰ ጠቃት ሁለት ፖሊሶች ተገድለዋል

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ በተፈጠረ ግጭት ሦስት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡

ሰላማዊ ሰዎች የተገደሉት በከተማዋ በተቀሰቀሰው ግጭት ላይ ፖሊስ ወደ ሕዝብ በከፈተው ተኩስ መሆኑን ሆርን ፈሪኩዌንሲ ያገኘው መረጃ ያመላክታል። ግጭቱ የተቀሰቀሰው መስከረም 17/2018 ዓ.ም ሲሆን በቀጣዩ ቀን መስከረም 18/2018 ዓ.ም ረፋድ ድረስ ዘልቋል።

የግጭቱ መነሻ “የሲናኖ ሴራ” የተባለው አካባቢው ባህላዊ የሽምግልና ሥረዓት የባለቤትነት ይገባኛል ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ አለመግባባት ነው ተብሏል።

በግጭቱ የሰው ህወይት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ “ማንንም ሊወክሉ በማይችሉ የተደራጁ” ያላቸው አካላት በከተማዋ በተወሰኑ መንደሮች ውስጥ ብጥብጥና ረብሻ ፈጽመዋል ብሏል፡፡

ግጭቱ ከመስከረም 18/2018 ረፋድ ወዲህ መርገቡ የተገለጸ ቢሆንም፣ አሁን አካባቢ በውጥረት ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል በጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሁለት ፖሊሶች ሲገደሉ፣ በአንድ አባል ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል፡፡ መስከረም 15/2018 በወልቂጤ ከተማ በሚገኘው በዞኑ ፖሊስ መምሪያ ላይ የመከላከያ ሰራዊት ዮኒፎርም የለበሱ ናቸው ተባሉ አካለት ጥቃት መፈጸማቸውን የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ጥቃቱ የፈጸሙት የተፈጸመው የመከላከያ ሰራዊት ዩኒፎርም በመልበስ የሰራዊት አባል መስለው በዞኑ ፖሊስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ዘልቆ በመግባት ነው ተብሏል፡፡ በመከላከያ ዪኒፎርን ተመሳስለው ወደ ፖሊስ መምሪያ ግቢ የገቡት አካላት በከፈቱት ተኩስ፤ ሁለት የፖሊስ አባላት ሲገደሉ አንድ መቁሰሉን መምሪያው አረጋግጧል።
የዞኑ አስተዳደር በመግለጫው ጥቃቱን “ይህ ድርጊት እጅግ አሳዛኝ፤ በመንግስትና በሕዝብ ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው” ብሎታል። የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ የጥቃቱን ፈጻሚዎች “ጽንፈኞች” ሲል የገለጻቸው ሲሆን፣ እነዚህን ኃይሎች በለውጥ አደናቃፊነት ወንጅሏቸዋል፡፡

መንግሥት የጀመረው ለውጥ “የማይዋጥላቸው ጥቂት ግጭት ናፋቂዎች ሂደቱን ለማደናቀፍ የተለያዩ የግድያና የዘረፋ ወንጀሎችን ሲፈጽሙ ቆይተዋልል። እየፈጸሙም ይገኛሉ” በማለት ወንጅሏል። ይህ ጥቃት ከቡታጅራው ግጭት ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይያያዝ እንደሆነ አመላካች ነገሮች የሉም፡፡

 
 

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *