በቀን ነሐሴ 28/2017 የመንግስት የጸጥታ አካላት ድል በር በሚገኘው የሸገር ራዲዮ ግቢ በመሄድ ሦስት ጋዜጠኞችን አስረው መውሰዳቸው ተሰምቷል፡፡ አንጋፋውን ጋዜጠኛ እሸቴ አስፋን ጨምሮ ትዕግስት ዘርይሁን እና ምንታምር ጸጋው በቁጥጥር ስር መዋላቸው የታወቀ ሲሆን ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ መለቀቁ ታውቋል፡፡
ከሳምንት በፊት ከተላለፈ ዜና ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ሳይውሉ እንዳልቀረ የተነገረው ጋዜጠኞች እና የቴክኒክ ባለሙያ በአሁኑ ሰዓት በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ማቆያ ስፍራ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በመንግስት የጸጥታ አካላት ጋዜጠኞች መታፈን እና ወደ እስር መጋዝ በአጭር ጊዜያት ውስጥ ይህ ለኹለተኛ ጊዜያት ሲሆን፤ እየጨመረ መምጣቱ ደግሞ ጉዳዩን አሳሳቢ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ የሸገር ራዲዮ የስራ ኃላፊዎች ምንም አይነት አስተያየትም ሆነ የጋዜጠኞችን እስር በሚመለከት መረጃ አልሰጡም፡፡










