Home / ፖለቲካ / የምክክር ኮሚሽኑ በአሜሪካ ብርቱ ተቃውሞ ገጥሞታል

የምክክር ኮሚሽኑ በአሜሪካ ብርቱ ተቃውሞ ገጥሞታል

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ያዘጋጀው የዲያስፖራ አጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረክ ብርቱ ተቃውሞ አስተናግዷል።

ኮሚሽኑ ቅዳሜ ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ ማዘጋጀት መድረክ ላይ ከውስጥ እሰከ አደባባይ ተቃውሞ ማስተናገዱን ሆርን ፍሪኩዌንሲ ሰምቷል። ኮሚሽኑ ባዘጋጀው ምክክር ላይ ከተሳተፉ ዲያስፖራዎች የገጠመው ተቃውሞ፣ “የመንግሥት አጀንዳ አስፈጻሚ ነው በሚል ነው።

የምክክሩ ተሳታፊዎች ኮሚሽኑ እያደረገ ያለውን ጥረት፣ “የመንግሥት ሥልጣን ለማራዘም” የሚመስል አካሄድ ተከተልሏ ብለዋል። ለዚህም ያቀረቡት ምክንያት የሀገር ውስጥ እየተካሄዱ ያሉ የእርስ በእርስ ጦርነትና ግጭቶችን መቀጠልና ችላ መባል ነው።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ ተቃውሞ የቀረበበት የምክክር ሂደቱ ገለልተኝነት አካታችነትና ውጤታማነት ላይ ጥያቄ ባላቸው የዲያስፖራ ወገኖች ነው። በኮሚሽኑ የሰሜን አሜሪካ ምክክር ላይ ያልተገኙ ዲያስፖዎች መድረኩ በተዘጋጀበት ሆቴል አካባቢ ተቃውሞ አሰምተዋል።

በኮሚሽኑ የምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ላይ የተገኙ ዲያስፖራዎችም፣ ከአዳራሽ ውጪ የተደረገበትን ተቃውሞ ኮሚሽኑ እንዴት እንደሚመለከተው ጥያቄ ቀርቦለታል።

በኮሚሽኑ ላይ ለቀረበው ተቃውሞ ምላሽ የሰጡት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አረአያ (ፕ/ር)፣ የኮሚሽኑ አላማ እንደተባለው “አንድ ግለሰብ፣ አንድ ፓርቲ፣ አንድ መንግሥት” ለማገልገል አይደለም ብለዋል። ኮሚሽኑ በሀገር ውስጥ የሚደረጉ የእርስ በእርስ ጦርነትና ግጭቶችን የማስቆም ኃላፊነት እንዳልተሰጠውም በመድረኩ ገልጿል።

ኮሚሽኑ በርካት ኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያን ዲያስፖራ በሚኖርበት ሰሜን አሜሪካ የምክክር አጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረክ፣ የተገኙት ተሳታፊዎች ውስን መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። ኮሚሽኑ የምክክር መድረኩን ያዘጋጀው በአካልና በዙም ዲጂታል አማራጭ ጭምር ነበር።

ይሁን እንጂ በአካል የተገኙት የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎችም ይሁን በዲጂታል አማራጭ የተሳተፉት ጥቂቶች ናቸው። በዲጂታል አማራጭ በምክክር መድረኩ ላይ የታደሙት ሰዎች ቁጥር ከ70 ያልበለጠ መሆኑን ሆርን ፎሪኩዌንሲ ከተሳታፊዎች ሰምቷል።

የምክክር ኮሚሽኑ የዲያስፖራውን ማኅበረሰብ አጀንዳ የማሰባሰብ ጥረቱ ተቃውሞ የገጠመው ቢሆንም፣ እንደ ከናዳ ባሉ ሌሎች ሀገራትም መድረክ አሰናድቷል። ይህንንም ተከትሎ በካናዳ ቶሮንቶ ኮሚሽኑ የሚኖረውን መርሃ ግብር ይፋ ማድረጉንም ተከትሎ ብርቱ ቁጣ እና ተቃውሞ አስቀድሞ አስተናግዷል፡፡ ሆርን ፍሪኩዌንሲ ያነጋገራቸው በቶሮንቶ እና አካባቢው የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንደተናገሩት በርካቶች እንደማይሳተፉ አቋም መያዛቸውን አሰታውቀዋል፡፡ ይሁን እንጂ ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል ደግሞ በስፍራው ተገኝተው ሞጋች ሃሳቦችንም ለመሰንዘር አስበዋል ብለዋል፡፡

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *