Home / ቢዝነስ / እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው ተሹመዋል

እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው ተሹመዋል

እዮብ ተካለኝ ቶሊና (ዶ/ር) በቅርቡ ከኃላፊነት በለቀቁት የቀድሞው የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ምትክ በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ 11ኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ በመሆን ተሹመዋል፡፡

እዮብ ከዚህ ቀደም በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ተቋማት በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉ እና ሲያገለግሉ የቆዩ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ሹመት አስቀድሞም የገንዘብ ሚንስትር ዲኤታ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአገር በቀል የማክሮኢኮኖሚ ኮሚቴ ውስጥም አባል በመሆን እያገለገሉም የገኛሉ፡፡

በትምህርት ዝግጅታቸውም አሜሪካን አገር ከሚገኘው ሜሪላንድ ዩንቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በፖቲካል ኢኮኖሚ ያገኙ ሲሆን በዛው በአገረ አሜሪካ ጆርጅ ዋሽንግተን ዩንቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡ በመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከመቐለ ዩንቨርሲቲ ማግኘታቸውን ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በዛሬው ዕለት ተጨማሪ ሹመት የሰጡ ሲሆን በሚንስትር ማዕረግ የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልገሎት ኃላፊ እናትአለም መለሰን ሾመዋል፡

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *