Home / ቢዝነስ / አየር መንገዱ ወደ ሁመራ በረራ ሊጀምር ነው

አየር መንገዱ ወደ ሁመራ በረራ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሁመራ መደበኛ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል።

አየር መንገዱ ወደ ሁመራ የሚያስጀምረው መደበኛ በረራው ከህዳር 10/2018 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑ ተጠቁሟል። ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ወደ ከሁመራ-አዲስ አበባ በሳምንት ሁለት በረራዎች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

አየር መንገዱ ወደ ሁመራ መደበኛ በረራ ለመጀመር የተዘጋጀው በአከባቢው ባለሥልጣናት ተደጋጋሚ ውትወታ በኋላ ነው ተብሏል። የአካባቢው ባለሥልጣናት አየር መንገዱ ወደ ሁመራ በረራ ቢጀምር የገበያ አዋጭነቱ አስተማማኝ እንደሆነ በመግለጽ ሲያግባቡ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል።

ባለሥልጣናቱ የማኅበረሰቡን የተራዘመ የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ሆርን ፍሪኩዌንሱ የጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ሰምቷል። የወልቃይት ሕዝብ በአውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ ለመብረርም ይሁን ለመመለስ፣ በየብስ ትራንስፖርት ከጎንደር-ሁመራ መጓጓዝ ይጠበቅበት እንደነበር ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል፡፡

የአካባቢው ማኅበረሰብ በአማራ ክልል በተከሰተው ጦርነት ጋር በተያያዘ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት የእንቅስቃሴ መስተጓጐል ገጥሞታል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የጎንደር-ሁመራ መስመር በተደጋጋሚ እገታዎችና የታጣቂዎች ጥቃት የሚፈጸምበት መሆኑ ሲገለጽ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

በተለይ ባለሥልጣናት በጎንደር-ሁመራ መስመር ለመጓዝ የመንገድ ደህንነት ቅድመ ጥናት ማድረግና ከፍተኛ እጀባ ያስፈልጋቸዋል። የአካባቢው ባለሥልጣናትና በወልቃይት የተሰማራው የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች በአማራ ክልሉ የጸጥታ ስጋት በአመዛኙ ወደ አዲስ አበበ፣ ጎንደርና ባህር ዳር የሚጓጓዙት በሄሊኮፕተር መሆኑን ለሆርን ፍሪኩዌንሲ የደረሱት መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

አየር መንገዱ የቀረበለትን ተደጋጋሚ ጥያቄ የገበያ አዋጭነቱን ተሳቢ በማድረግ መደበኛ በረራ ለመጀመር መወሰኑ ተገልጿል። የአዲስ አበባ-ሁመራ በረራ ዋጋ ተመን ምን ያክል እንደሆነ ለጊዜው አየር መንገዱ የትኬት መሸጫ ዋጋውን ይፋ አላደረገም፡፡

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *