Home / ፖለቲካ / ማርኮ ሩቢዮ ከጠ/ሚር ዐቢይ ጋር በስልክ ተነጋገሩ

ማርኮ ሩቢዮ ከጠ/ሚር ዐቢይ ጋር በስልክ ተነጋገሩ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል፡፡

የስልክ ውይይታቸውም በአፍሪቃ ቀንድ ለሚኖረው የሰላም መሰረት የአሜሪካን እና የኢትዮጵያን የጋራ ቁርጠኝነት ላይ መሰረት ያደረገ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከቀናት በፊት የአሜሪካ በአፍሪቃ ኮማንድ (አፍሪኮም) ዋና ኮማንደር ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪቃ አገራትን መጎብኘታቸው የሚታወስ ሲሆን በኢትዮጵያ ከጠ/ሚር ዐቢይ እንዲሁም ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር በቀጠናው የሰላም እና ደኅንነት ጉዳይ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለው መካረርም በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እና ቀጠናው ወደ ተጨማሪ ግጭት እና ቀውስ እንዳይገባም ጥንቃቄ እንዲደረግ መምከራቸውን ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን በወቅቱ አስታውቀዋል፡፡

ከቀጠናው ሰላም ጋር በተገናኘም የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሱዳን ያለውን ግጭት ለማስቆም ቁርጠኝነት ማሳየታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ማርኮ ሩቢዮ በተመሳሳይ የጸጥታ እና መረጋጋት ጉዳይ እንዲሁም በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት እና በአገር ውስጥ ለተደረገው የኢኮኖሚ ሪፎርም እንዲሁም ሁለቱ አገራት ለሚኖራቸው የንግድ ትስስር ዙሪያ ያደረጉበት የስልክ ውይይት በወርሃ ሐምሌ ከተደረገ በኋላ ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *