Home / ፖለቲካ / እስራኤል ለሶማሌላንድ ይፋዊ የአገርነት እውቅና ሰጠች

እስራኤል ለሶማሌላንድ ይፋዊ የአገርነት እውቅና ሰጠች

እስራኤል ለራስ ገዟ ሶማሌላንድ ይፋዊ የሉዓላዊ ሀገርነት እውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። እስራኤል በዛሬው ዕለት ለሶማሌላንድ እውቅና መስጠቷን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታንያሁ አስታውቀዋል። እስራኤል የምሥራቅ አፍሪካ ቁልፍ አጋር ትሆነኛለች ላለቻት ሶማሊላንድ እውቅና የሰጠችው፣ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አነሳሽነት ነው ተብሏል።

እውቅናውን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እና የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዱራህማን መሐመድ አብዱላሂ ስምምነት በመፈራረም ይፋ አድርገውታል። መሪዎቹ ከያሉበት ሆነው በፈረሙት ስምምነት በቀጣይም አብረው በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን መሰረት ጥለዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት የተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጀምሩም መሪዎቹ አስታውቀዋል እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እውቅና የሰጧት ሶማሊላንድ ፕሬዝዳን በእስራኤል ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጋብዛቸዋል።

እስራኤል እውቅና ከሰጠታች ሶማሊላንድ ጋር በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂ እና ሌሎች ዘርፎች መዋዕል ነዋይ ማፍሰሷም እንደምታጠናክር ተጠቁሟል። እስራኤል አክራሪ እስላማዊ ታጣቂ ቡድኖችን የመዋጋት አቅሟን ለማጠናከር በሶማሊላንድ የጦር ሰፈር እንደምትገባ ይጠበቃል።

ከእስራኤል ቀጥሎ አሜሪካ ለሶማሊላንድ እውቅና ልትሰጥ እንደምትችል እየተጠቆመ ነው። የእስራኤል እውቅና መስጠት የአብረሃም ስምምነትን በመጥቀስ በትራምፕ አነሳሽነት የተሰጠ መሆኑን መገለጹን ተከትሎ፣ በቀጣይ ደግሞ የአሜሪካ ውሳኔ በሱማሌላንድ እውቅና በኩል ከወዲሁ ተገማች ሆኗል።

የመጀመሪያ ይፋዊ እውቅና ከእስራኤል ያገኘችው ሶማሊላንድ፣ ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟ ይታወሳል። ስምምነቱ ሶማሊላንድ ከአዲስ አበባ ለምታገኘው እውቅና፣ በሊዝ ውል ላይ የተመሰረተ የባህር በር ለኢትዮጵያ በመስጠት ላይ የተመሰረተ ነበር።

ስምምነቱ አደጋ በዲፕሎማሲያዊ ጫና በመርታት በተቀመጠለት ጊዜ ሳይፈጸም እስከአሁን ቢዘልቅም በቱርክ አንካራ የተፈረመው የአዲስ አበባ እና የሞቃዲሾ ስምምነት ውሉን እንዲፈርስ እንዳደረገውም ይነገራል። የእስራኤልን እውቅና መስጠት ተከትሎ፣ ስምምነቱ ነፍስ ሊዘራ እንደሚችል ይጠበቃል።

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *