Home / ማህበራዊ / በአዲስ አበባ ከተማ አረቄ ቤቶች ይዘጋሉ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አረቄ ቤቶች ይዘጋሉ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው

የአዲስ አበባ መስተዳደር የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት በከተማ አስተዳደሩ ውስጠ የሚገኙ የአረቄ ቤቶች እና ቢንጎ ማጫወቻ ስፍራዎች ይዘጋሉ ተብሎ በኃላፊዋ የተገለጸው መረጃ ስህተት መሆኑን ቢሮው ለሆርን ፍሪኩዌንሲ አስታውቋል፡፡

ቢሮው በተሰራጨው መረጃ መሰረት ስብሰባ ላይ መሆኑን የታወቀ ሲሆን ይህ ውሳኔ በስራው ላይ በዋናነት ደግሞ በአረቄ መሸጥ ላይ ተሰማርተው ሕይወታቸውን የሚመሩ ሰዎችን ያላገናዘበ ነው ሲልም አክሎ ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ አረቂ ቤቶችን እና ቢንጎ የተሰኘውን የጨዋታ (ጌም) ዓይነት በሙሉ ከዚህ በኋላ አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ ማሳሰቡን ተከትሎ በርካታ አስተያቶች ከሕዝብ ዘንድ እንደተሰጠ ቢሮው አስታውቋል፡፡

ይህንን ውሳኔ ተከትሎ በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ከፍተኛ ቅሬታ እያቀረቡ ነው። የቢዝነስ ባለቤቶቹ አረቂ ቤት እና የጌም ዞን በመክፈት ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች የሥራ ዕድል እየፈጠሩ መሆኑን ገልጸው፤ ንግዳቸው እንዲዘጋ መወሰኑ “ጎዳና እንድንወጣ ተፈርዶብን ነው” የሚል ከፍተኛ ቅሬታ አቅርበዋል።

በዘርፉ የተሰማሩ ግለሰቦችን ያነጋገርን ሲሆን፣ የከተማዋ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ እና የደንብ ማስከበር አካላት አረቂ ቤቶችን እንዲዘጉ ሲነግሯቸው፣ የንግድ ፈቃዳቸውን እንዲለውጡ አስገዳጅ ትዕዛዝ እንደሰጡባቸውም ተናግረዋል።

እነዚህ ነጋዴዎች “የንግድ ፈቃድ ለውጠን ሌላ ስራ ውስጥ ለመሰማራት አቅማችን አይፈቅድም” በማለት ቅሬታቸውን አሰምተዋል። መንግሥት የተለየ ድጋፍ ሊያደርግላቸው ካልቻለ ለከፍተኛ ችግር እንደሚጋለጡም አስጠንቅቀዋል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ከዚህ ቀደምም አረቂ እና ጠላ ቤቶችን ሲያሽግ እንደነበር አስታውሶ ነበር፤ ይህም የሆነው የሽብር መፍጠሪያ ስፍራ እየሆኑ በመቸገሩ መሆኑን ገልጾ ነበር። በተለይም ከአረቂ ቤቶች የሚከፈቱት ሙዚቃዎችም ግጭት ቀስቃሽ እና ብሔርን ከብሔር ሊያጋጩ የሚችሉ ናቸው የሚል ክስ ቀርቧል።

አሁን በይፋ እንዲዘጋ የተወሰነው አረቂ እና ቢንጎ ቤቶች ቢሆኑም፣ በቀጣይነት ጠላ ቤትን እና ሌሎች ግጭት ሊቀሰቅሱ ይችላሉ ተብለው የታሰቡ የንግድ ዘርፎችን በሙሉ ለመዝጋት ዕቅድ እንዳለ ተመላክቷል።

በዘርፉ የተሰማሩት ማኅበረሰቦች ግን ከፍተኛ ቅሬታቸውን ማሰማታቸውን ቀጥለዋል።

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *