አሜሪካ ከፈረንጆች ጃንዋሪ 21 ጀምሮ ተግባራዊ የሚድረ የቪዛ እገዳ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ75 አገራት ላይ ተግባራዊ አድርጋለች። የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይን ዋቢ አድርገው በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደዘገቡት፤ የወቅቱ የአሜሪካ አስተዳደር በስደተኞች ዙሪያ ተግባራዊ እያደረገ ያለውን ፖሊሲ ተከትሎ ይህ እገዳም እንደተላለፈ ለማወቅ ተችሏል።
የቪዛ እገዳው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ በውል ባይታወቅም ውሳኔው ተግባራዊ ከሚሆንበት ቀን ጀምሮ በተጠቀሱት አገራት ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ኢምባሲዎች የቪዛ አገልግሎት አይሰጡም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢምግሬሽን ጉዳይ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ የሚገኘው የትራምፕ አስተዳደር ቀጣይ እርምጃዎችንም ሊያስተላልፍ እንደሚችል ይጠበቃል።











