በአሜሪካ የአስፈጻሚው አካል ውሳኔ ቁጥር 14362 መሰረት አሜሪካ በግብጽ፣ ዮርዳኖስ እና ሊባኖስ የሚገኘውን የሙስሊም ወንድማማቾች የተሰኘውን ስብስብ በአሸባሪነት መፈረጇ ይፋ ተደርጓል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው መስሪያ ቤቱ በሊባኖስ የሚገኘውን የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድንን እንዲሁም ቅርንጫፉን አመራር መሐመድ ፋውዚ ታቆሽን በልዩ ሁኔታ ዓለም አቀፍ ሽብርተኛ ብሎ መፈረጁ የታወቀ ሲሆን፤ የግብጽ እና የዮርዳኖስ ቅርንጫፍ የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድን ደግሞ በአሜሪካ የግምጃ ቤት በሽብርተኝነት መፈረጁን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
ይህ ውሳኔ አሜሪካ በቡድኑ ላይ ለምትወስደው ቀጣይነት ላለው እርምጃ እንደ ጅማሮ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል የተጠቀሰ ሲሆን አሜሪካ የሙስሊም ወንድማማቾችን የግቢ ምንጭን ለማድረቅ እና በቡድኑ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ማንኛውንም አይነት መንገድ እንደምትጠቀም በመግለጫው ተጠቅሷል።












