Home / ፖለቲካ / የጠቅላይ ሚንስትሩ አዲስ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

የጠቅላይ ሚንስትሩ አዲስ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ‘የመደመር መንግሥት’ የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ነገ መስከረም 6/2017 ዓ.ም እንደሚመረቅ ሆርን ፍርኩዌንሲ ሰምቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የጻፉት አራተኛ መጽሐፍ በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ምርቃቱ እንደሚካሄድ ታውቋል። የመጽሐፍ ምርቃት ፕሮግራሙን በደመቀ ሁኔታ እንዲካሄድም ጊዜ ተወስዶበት እንደተዘጋጀ ተረድተናል። በጥብቅ የደህንነት ጥበቃ ተዘጋጅቷል በተባለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጽሐፍ ምረቃ መድረክ ላይ ስልክ ጭምር ይዞ መግባት አይቻልም ተብሏል።

በመድረኩ ላይ የሚገኙ ተጋባዦች በልዩ ሁኔታ ከተፈቀደላቸው ውጭ ምንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ ነገር ይዘው መግባት አይፈቀድላቸውም ተብሏል።

በመድረኩ ላይ ክልልሎች ጨምሮ አብዛኛዎቹ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዲገኙ ጥሪ ደርሷቸዋል ተብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መደመር፣ የመደመር መንገድና የመደመር ትውልድ የተሰኙ መጽሐፍትን በተከታታይ መጻፋቸው ይታወሳል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍልፍስፍና እንደሆነ የሚነገርለት የመደመር ጽንሰ ሀሳብ መንግሥታዊ አቋም ወደመሆን እንደተሸጋገረም ይነገራል። አዲሱን መጽሐፋቸውን አስመልክቶ ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ቃለ መጠይቅ የመደመር ሀሳብ፣ የሚመሩት መንግሥት አቋም መሆኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መደመር ከግለሰብ ሀሳብነት እስከ መንግሥታዊ አቋምነት ደርሳሉ ቢሉም፣ ጽንስ ሀሳቡ ላይ ጥያቄ ይነሳበታል። ምንም እንኳን መሪዎች የሚያመነጯቸው ሀሳቦች በሀገር ደረጃ መቀንቀናቸው የተለመደ ቢሆንም፣ መሪዎች አንደ ግለሰብ የሚያመነጫቸው አስተሳሰቦች ሁሉንም ሀገራዊ ፖሊሲዎች ሊበይኑ እንደማይችሉ ይነገራል። ከዚህ አንጻር የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ የመደመር ጽንስ ሀሳብም መንግሥታዊ አቋም ወደመሆን ደረጃ ካደገ በአግባቡ መፈተሽ እንዳለበት ይታመናል።

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *