Home / ማህበራዊ / ‹‹ለተፈናቃዮች በማኅበራዊ ሚዲያ ገቢ ማሰባሰብ አይቻልም›› መንግሥት

‹‹ለተፈናቃዮች በማኅበራዊ ሚዲያ ገቢ ማሰባሰብ አይቻልም›› መንግሥት

በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች ተፈናቅለው በመጠለያ ለሚገኙ ወገኖች በማኅበራዊ ሚዲያ የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ እንዲቆም መንግሥት አስጠነቀቀ። መንግሥት እውቅና ያልሰጠው የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ሕገ ወጥ መሆኑን ኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም አስታውቀዋል።

ኮሚሽነሩ በመጠለያ ጣቢያዎች ለችግር የተጋለጡ ተፈናቃዮችን ለመርዳት የተጀመረውን ገቢ የማሰባሰብ ዘመቻ መንግሥት እንደማዪውቀው ገልጸዋል። ሽፈራው አያይዘውም ኮሚሽኑ ዕውቅና ባልሰጠበት ሁኔታ በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት የሚደረጉ የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻዎች ሕገ ወጥ ናቸው፣ በገቢ ማሰባሰብ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችንም ማስተባበራቸውን እንዲያቆሙ አስጠንቅቀዋል።

ኮሚሽነሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገቢ የማሰባሰብ ዘመቻዎችን የሚያስተባብሩ አካላትን ያስጠነቀቁት፣ በትግራይ ክልል ሕጻጽ መጠለያ ጣቢያ በተከሰተው የተፈናቃዮች ችግር ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ ነው። በሕጻጽ ለተፈጠረው የተፈናቃዮች የሰብዓዊ ድጋፍ እጥረት ህወሓትን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፣ ሆን ተብሎ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ትኩረት ለመሳብ የተወጠነ ‘ድራማዊ ፕሮፓጋንዳ’ በማለትም ገልጸውታል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች ለተፈናቀሉና እርዳታ ለሚሹ ወገኖች፣ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ገቢ መሰብሰብ የተለመደ ነው። መንግሥት በዚህ ወቅት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በማኅበራዊ ሚዲያ የሚደረጉ የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻዎችን ሕገ ወጥ በማለት እንዲቆሙ የወሰነበት ምክንያት በውል አልተገለጸም።

ከሰሞኑ በትግራይ ክልል ሕጻጽ እና በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች በማኅበራዊ ሚዲያ ሰፊ ዘመቻ እየተካሄደ ነበር። መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያ የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻዎችን መገደቡ፣ የተቸገሩ ወገኖች እንዳይረዱ በር እንደሚዘረጋ ከወዲሁ እየተገለጸ ነው።

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *