Home / ፖለቲካ / የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ እና ጎረቤት አገር መካከል ያለውን መካረር እንዲረግብ ጠየቀ

የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ እና ጎረቤት አገር መካከል ያለውን መካረር እንዲረግብ ጠየቀ

የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በኩል ያስታወቀ ሲሆን ድንበር ዘለለ መካረሮች እንዲረግቡም ጠይቋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ እንዳሳሰበውም ጨምሮ ገልጿል።

የካናዳ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በቀጠናው ያለው መካረር እንዲረግብ እና ሁሉም አካላት ነገሮችን ከማባባስ እንዲቆጠቡም አሳስቧል። በፍጥጫ ውስጥ ያሉትን አካላት በግልጽ ያላስቀመጠው መስሪያ ቤቱ፤ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ለገባችበት እሰጣገባ መልዕክት ሆኖ ተቀምጧል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ እና ጎረቤት አገር ኤርትራ የገቡበት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻከር ወደ ጦር መማዘዝ ማደጉን ተከትሎ ሙሉ በሙሉ ወደ ለየለት ጦርነት እንዳይገቡ በርካታ አገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ስጋታቸውን እያስተጋቡ ይገኛሉ።

አዲስ አበባ እና አስመራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው ግንኙነት ኢምባሲዎቻቸውን ወደ መዝጋት እና ከቅርብ ቀናት ወዲህ ደግሞ አልፎ የሚሰሙ የከባድ መሳሪያ ተኩሶችን ማስተናገድ ጀምረዋል። ይህ ደግሞ በቀጠና አዲስ እና ከፍተኛ ደም አፋሳሽ ግጭት እንዳይፈጥር ተሰግቷል። ከካናዳ በተጨማሪ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ ባደረጉት ቆይታ ሁኔታዎችን በማርገብ ሂደት ላይ እንዲያተኩሩ አሳስበዋል።

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *