የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለመጪዎቹ አራት ወራት ለባንኮች የውጭ ምንዛሪ ጨረታ 840 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያቀርብከወዲሁ አስታውቋል።
ባንኩ በተያዘው 2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ሁለተኛ ሩብ ዓመት ለማቅረብ ያሰበውን የዶላር መጠን ይፋ ያደረገው፣ የውጭምንዛሪ ዋጋ እየጨመረ ባለበት ወቅት ነው። ባንኩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የውጭ ምንዛሪ ጨረታውከጥቅምት 3/2019 ዓ.ም ጀምሮ በየሁለት ሳምንቱ ክፍተት የሚካሄድ ይሆናል።
በስድስት ዙር በሚካሄደው በእያንዳንዱ የጨረታ ቀን 140 ሚሊዮን ዶላር ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን፣ የጨረታ ቀናቱምከወዲሁ ታውቀዋል። ጥቅምት ሦስት፣ ጥቅምት 17፣ ኅዳር አንድ፣ ኅዳር 15፣ ኅዳር 29፣ ታኅሣሥ 13/2019 ዓ.ምበተከታታይ በየአንዳንዱ ቀን 140 ሚሊዮን ዶላር ለባንኮች ጨረታ ይቀርባል።
ብሔራዊ ባንክ የሚቀጥሉትን ወራት የዶላር ጨረታ አቅርቦት አስቀድሞ ይፋ ያደረገው፣ የውጭ ምንዛሬ ማሻቀቡን ለማረጋጋት በማሰብ መሆኑ ተጠቁሟል።
የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ከአንድ ወር ወዲህ በመደበኛም፣ በጥቁር ገበያም ከፍተኛ የተባለውን ጭማሪ አሳይቷል።
ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የሰጣቸው የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች፣ ዛሬ መስከረም 26/2019 አንድ ዶላር እስከ 186 ብር እየገዙነው። መሸጫ ቢሮዎቹ አሁን ላይ ከ184 እስከ 186 ብር በመግዛት፣ እስከ 188 ብር ድረስ ለደንበኞቻቸው ይሸጣሉ።
ባንኮች ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚላክ ዶላር እስከ 180 ብር እየመነዘሩ ነው። በተመሳሳይ ለደንበኞቻቸውየሚያቀርቡበት ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ አሻቅቧል።
እንደ አቢሲኒያ፣ አዋሽ፣ ኦሮሚያ ያሉት ባንኮች በየፊናቸው ባለሙት የውጭ ምንዛሬ መላኪያ መተግበሪያ አንድ ዶላር 180 ብር እገዙ ነው። በተመሳሳይ የባንክ አገልግሎቶችን እየሰጠ የሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም፣ በቴሌብር ሐዋላ በኩል አንድ ዶላር180 ብር እየገዛ ይገኛል።
መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ፣ ሲቢኢ ኮኔክት (CBE Connect) በተሰኘ የውጭ ምንዛሬ መላኪያመተግበሪያው አንድ ዶላር በ177 ብር እየገዛ ነው።
በሌላ በኩል የጥቁር ገበያው ዋጋ ከመደበኛው እስከ 18 በመቶ ብልጫ አሳይቷል። አሁን ላይ አንድ ዶላር እስከ 197 ብርድረስ እየተሸጠ ነው።












