Home / ፖለቲካ / ከትግራይ ክልል መድኃኒት እና የሕክምና ግብዓቶች ወደ ኤርትራ መወሰዳቸው ታወቀ

ከትግራይ ክልል መድኃኒት እና የሕክምና ግብዓቶች ወደ ኤርትራ መወሰዳቸው ታወቀ

ከትግራይ ክልል ከፍተኛ መጠን ያለው መድኃኒት እና የሕክምና ግብአት ወደ ኤርትራ ተጭኖ መውሰዱን ምንጮች ለሆርንፍሪኩዌንሲ ገልጸዋል።

የሕወሓት አመራሮች ከትግራይ ክልል ከፍተኛ መጠን ያለው መድኃኒት፣ የሕክምና ግብዓቶች፣ የቢሮ መገልገያዎችንናበርካታ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤርት መውሰዳቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን አስታውቀዋል። በርካታ የሕዝብ መገልገያዎች ወደ ኤርትራ ተጭነው የተወሰዱት አስቀድሞ በታሰበበት ሁኔታእንደሚመስል ተጠቁሟል።

መጠነ ሰፊ የሕዝብ መገልገያዎች ወደ ኤርትራ መወሰዳቸው የታወቀው፣ የመንግሥት ኃይሎች የትግራይ ከተሞችንከተቆጣጠሩ በኋላ ነው ተብሏል። መከላከያ ሠራዊት በተቆጣጠራቸው አካቢበዎች የፖለቲካ ሥራ እንዲሰሩ ከፌዴራልመንግሥት የተላኩ አካላት መጠነ ሰፊ ንብረት መዘረፉን ሪፖርት ማድረጋቸውን ተከትሎ የመድኃኒት እና የህክምና አገልግሎት መሳሪያዎች መዘረፋቸውን ይፋ አድርገዋል።

ምንጮች እንደሚሉት ከ700 በላይ ተሽከርካሪዎች ወደ ኤርትራ ተወስደዋል። ተሽከርካሪዎቹ ወደ ኤርትራ ሲወሰዱ፣መድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶችን ጨምሮ የሕዝብ መገልገያዎች መጫናቸው ተጠቁሟል።

የሕወሓት አመራሮች የሕዝብ መገልገያዎችን ወደ ኤርትራ ማሸሻቸውን ተከትሎ፣ የተረፈው የመንግሥት ንብረት ለዘረፉመጋለጡ ተገልጿል። ማኅበረሰቡ የሕዝብ መገልገያዎች ተጭነው ሲወሰዱ ማየቱ የተገለጸ ሲሆን፣ ሕወሓቶች ከተሞችንጥለው ከወጡ በኋላ የተረፈው ንብረት ተዘርፏል ተብሏል።

በሕወሓት ተጭኖ ወደ ኤርትራ የተወሰደውን እና የተዘረፈውን የሕዝብ መገልገያ መልሶ መተካት፣ ከባድ ሊሆንእንደሚችል ተጠቁሟል።

Tagged:

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *