በጂቡቲ የባሕር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ ቢያንስ 139 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሕይወታቸው ማለፉንየተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ።
ከጎረቤት ሀገር ጂቡቲ ወደ የመን እየተጓዘ የነበረ ጀልባ ተገልብጦ ህጻናትን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ስደተኞች ለሕልፈት መዳረጋቸውን ተቋሙ አስታውቋል። ጀልባዋ በጠቅላላው 305 ስደተኞችን አሳፍራ እንደነበር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ጀልባው በተገለበጠበት የባህር ዳርቻ የአብዛኞቹ ማቾች አስከሬን ሲገኝ፤ 84 ሰዎች የደረሱበት ባለመታወቁ በሕይወትየመገኘታቸው ጉዳይ አስጊ ሆኗል። ከአደጋው በሕይወት የተረፉት ወደ 82 የሚሆኑ ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊያንመሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ሟቾችም ኢትዮጵያ መሆናቸው ታውቋል።
የበርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ሕይወት የቀጠፈው አደጋ ያጋጠመው፤ ጀልባው ከአቅም በላይ ሰው መጫኑ መሆኑንበሕይወት የተረፉት ሰዎች ገልጸዋል።
የተመድ የፍልሰተኞች ድርጅት ኢትዮጵያዊያን የተሻለ ኢኮኖሚ ፍለጋ በወጡበት በባህር ላይ ሕይወታቸውን እያጡ ነውብሏል። በተደጋጋሚ የሚሰማው የስደተኝች ሞት እንደ ተለመደ ነገር መታየት እንደሌለበትም አሳስሷል።
የዓመቱ ከአፍሪካ ቀንድ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በጂቡቲ በኩል ባብ ኤል-ማንደብን ተሻግረው ወደ የመንናከዚያም ወደ የባሕረ ሰላጤ አገሮች ለመድረስ የሚጠቀሙበት ነው። የቀጠናው ስደት ግፊት የጨመረው ድህነት፣አለመረጋጋትና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ በማየሉ ነው ተብሏል።
ባለፈው የፈረንጆቹ 2025 ብቻ በጂቡቲ ባህር ዳርቻ ላይ ከ900 በላይ ስደተኞች ሞተዋል። አብዛኞቹ ሟቾች ኢትዮጵያዊያንስደተኞች መሆናቸው በየጊዜው የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።












