ከፌደራል መንግሥት ጎን የተሰለፈው እና ራሱን ሓራ መሬት ወይም የትግራይ ሰላም ኃይል ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን፣በራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ እያስተጓጎሉ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
ከመንግሥት ጎን ተሰልፎ ሕወሓትን እየተዋጋ የሚገኘው የሓራ መሬት ታጣቂዎች የራያ ቀጠናዎችን የምናስተዳድረው እኛነን በሚል ከተሞችን እየተቆጣጠሩ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ሕወሓት በአካባቢው ባደረሰው ጥቃት የተፈናቀሉ የአማራ ማንነትጥያቄ ያላቸውን ወገኖች ተመልሰው ወደ ራያ እንዳይገቡ ተኩስ በመክፈት ኹከት ፈጥሯል ተብሏል፡፡
የሓራ መሬት ታጣቂዎች አላማጣ ከተማን ከእኛ ውጪ የሚቆጣጠር የአካባቢ ኃይል አይኖርም በሚል “የራያ ዘብ” በሚል ራሱን በሚጠራው እና በአካባቢው መንግስት እውቅና እና ድጋፍ የተቋቋመው ቡድን ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ተከትሎ፣ከባድ ውጥረት ተፈጥሯል፡፡ ከዚህ ቀድም በሕወሓት ጥቃት የተፈናቀሉ 70 ሺህ ገደማ የአማራ ተወላጆች ወደ ራያሲመለሱ፣ በተፈጠረው ግጭት ወደ ቆቦ መመለሳቸውን መረጃውን ለዝግጅት ክፍላችን ያደርሱን ምንጮች ተናግረዋል።
ፌደራል ፖሊስ ከትላንት ጀምሮ በራያ አላማጣ ከተማ ኮማንድ ፖስት ያወጀ ቢሆንም፣ የታጣቂዎቹ ግጭት ከፍተኛውጥረት ፈጥሯል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ ከፌራል ፖሊስ እና ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ውጪ በከተማ ውስጥ ታጥቆ መንቀሳቀስየተከለከለበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይሁን እንጂ የሓራ መሬት ታጣቂዎች ከመከላከያ ጎን ተሰልፈን በመዋጋት አካባቢን ነፃ ያወጣነው እኛ ነን በሚል አስተዳደሩንለመቆጣጠር እየሞከሩ ነው ተብሏል፡፡ ከዚህ ቀደም ጫካ የገባው የአካባቢው አስተዳደርም ወደ ከተማ ተመልሶአስተዳደሩን ለመረከብ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ የሓራ መሬት ታጣቂዎች ጥቃትመፈጸማቸውን እና ተፈናቃዮች እንዳይመለሱ መንገድ መዝጋተቸውን አስታውቋል፡፡ በሕወሓት ጥቃት ከቀየው ተፈናቅሎበራያ ቆቦና ሰቆጣ ይኖር የነበረው ህዝብ አካባቢው ነፃ መውጣቱን ተከትሎ፣ በዛሬው ቀን 23/01/2019 ዓ.ም ወደ ቀየውበመመለስ ላይ እያለ በሓራ መሬት ታጣቂዎች ወደ ቀየው እንዳይመለስ ተኩስ ተከፍቶበት መንገድ ላይ ታግዷል ብሏል።
በራያ ማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳይ ላይ የፌዴራል እና የክልሉ መንግሥት ግልጽ አቋምና ተቋማዊ እርምጃእንዲወስዱ ጠይቋል፡፡ ሕዝቡ ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ጫናዎችን ለማስቀረት የአስተዳደር ጉዳዮች በሕግ አግባብእንዲመሩ የጠየቀ ሲሆን፣ መከላከያ ሠራዊትም ሰላም እንዲያስከበር ጥሪ አቅርቧል፡፡












