የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ግብጽ መካከል እየተካረረ የመጣውን ግንኙነት ምክንያት በማድረግ ባወጣው መግለጫ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው እንደሚገኝ እና ሦስቱም አባል አገራት ችግሩን ከሚያባብሱ መግለጫዎች ተቆጥበው በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ልዩነቶቻቸውን እንዲፈቱ አሳስበዋል።
ኮሚሽኑ ሦስቱም አገራት ሰላማዊ መንገድን ለመምረጥ እና ውጥረቱን ለመቀነስ በሚያደርጉት ሂደት ውስጥ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል።
ኢትዮጵያ በአስመራ ያለውን ኢምባሲዋን መዝጋቷን ባስታወቀችበት ቀን አስር የኤርትራ ዲፕሎማቶችን በ48 ሰዓት ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቧ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የኤርትራ መንግስት ባወጣው ምላሽ የኢትዮጵያን መንግስት በግልጽ በመኮነን የቀይ ባህርን አጀንዳ በማንሳት የኢትዮጵያን መንግስት ጠብጫሪ ሲልም ገልጿል። አያይዞም በኤርትራ በኃይል የመንግስት ለውጥ ለማምጣት እና የአገር ውስጥ አለመረጋጋት ለመፍጠር የሚሰሩ የታጠቁ አካላትንም ይደግፋል ሲል የኢትዮጵያ አቻውን ወንጅሏል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ ዲፕሎማቶች በተጨማሪም በአዲስ አበባ የግብጽ ኢምባሲ ውስጥ አህመድ ሞህረም አህመድ የተባሉ ዲፕሎማትን በ48 ሰዓታት ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ መወስኑንም አስታውቋል።










