Home / ዜና / ቀይ መስቀል 161 ሰዎችን ከትግራይ ክልል ማውጣቱን አስታወቀ

ቀይ መስቀል 161 ሰዎችን ከትግራይ ክልል ማውጣቱን አስታወቀ

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የአየር መንገድ ሠራተኞችን እና የፌደራል ፖሊስ አባላትን ጨምሮ 161 ሰዎችንከትግራይ ክልል ማውጣቱን አስታውቋል፡፡

ኮሚቴው ከትግራይ ክልል ካስወጣቸው መካከል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች፣የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ሠራተኞችን ከእነ ቤተሰቦቻቸው፣ እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች እና የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማኅበር አባላት እንደሚገኙበት ገልጿል፡፡ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ 161 ሰዎችን ከትግራይ ያወጣው፣ከሁሉም ባለድርሻ አካላት በቀረበለት ጥሪ እና በሰጡት ምላሽ መሰረት የገለልተኛ ሚናው በመጠቀም መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከትግራይ ክልል የወጡት ሰዎች የተጓጓዙት በየብስ ትራንስፖርት ወደ አፋር ክልል ሰመራ መሆኑን ኮሚቴው ጠቁሟል፡፡ከትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ወደ አፋር ክልል ሰመራ የተደረገው ጉዞ የቀይ መስቀል አርማ ምልክት በተደረገባቸውአውቶቡሶች እና በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ሠራተኞች እጀባ መፈጸሙ ተመላክቷል።

ኮሚቴው በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ ለአደጋ ተጋለጭ የሆኑ ሰዎችን ከግጭት ቀጠናዎች ማውጣቱን እንደሚቀጥልጠቁሟል፡፡ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ በሚሆንበት ጊዜ እና ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ተባባሪ በሚሆኑበትጊዜ ሁሉ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ገልጿል።

Tagged:

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *