Home / ፖለቲካ / ትግራይ ክልልን በጊዜያዊነት የሚያስተዳድር የ “ባለአደራ” አስተዳደር ተቋቋመ

ትግራይ ክልልን በጊዜያዊነት የሚያስተዳድር የ “ባለአደራ” አስተዳደር ተቋቋመ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት የፌደራል መንግሥቱን አቅጣጫ የሚያስፈጽም የትግራይ ክልል ባለአደራአስተዳደር አቋቁመዋል፡፡

የባለአድራ አስተዳደሩ የተቋቋመው ሦስት ሳምንት ያስቆጠረው የሕወሓት እና የመንግሥት ጦርነት ተጠናቋል በሚል ነው፡፡ዐቢይ የስድት ወር ዕድሜ ያለውን የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር የሚመሩ ባለሥልጣናት ሹመትም ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ዛሬ ባውጣው መግለጫ፣ “የህወሓት አመራር ለአራተኛ ጊዜ የጀመረው አውዳሚ ጦርነት፣ለአራተኛ ጊዜ በሕወሐት ሽንፈት ተጠናቋል” ብሏል። ፌደራል መንግሥት “ጦርነቱ ተጠናቋል” በማለት በይፋ ያወጀው፣በትግራይ እሰከ ኤርትራ ድንበር የዘለቀ ውጊያ መቀጠሉ በሚሰማበት ወቅት ነው፡፡

የፌደራል መንግሥት የጦርነቱ መጠናቀቅ በይፋ አውጆ ባለአደራ አስተዳደር ያቋቋመው፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እናአጋሩ የትግራይ ሰላም ኃይል የትግራይ ዋና ዋና ከተሞችን ከተቆጣጠሩ በኋላ ነው፡፡ ምንም እንኳን መከላከያ እሰከ ኤርትራድርንበር ድረስ ዋና ዋና ከተሞችን የተቆጣጠረ ቢሆንም፣ የሕወሓት ታጣቂዎች በሚንቀሳቀሱባቸው ገጠራማአካባቢዎች ውጊያ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

ለፌደራል መንግሥት ተጠሪ የሆነው ባለአደራ አስተዳደርን ለቀጣዮቹ ስድት ወራት የሚመሩ ባለሥልጣናት የተሰየሙ ሲሆን፤ በፕሪቶቶሪያው ስምምነት ወቅት የህወሓት ተደራዳሪ የነበሩት፣ አሰፋ አብርሃ የባለአደራ አስተዳደሩ የአስተዳደርእና የሕዝብ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነዋል፡፡ ⁠

ዶክተር ቴዎድሮስ የባለአደራው የኢኮኖሚ እና መልሶ ግንባታ ዋና አስፈጻሚ ረዳኢ ኃለፎም የፖለቲካ እና ሕዝብ አደረጃጀትዋና አስፈጻሚ፣ እንዲሁም ዶክተር ሽሻይ አማረ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ በመሆን ተሹመዋል።

የመንግሥት አጋሩ የትግራይ ሰላም ኃይል አዛዥ ብ/ጄ ገብረእግዚአብሄር በየነ (ወዲ አንጥሩ) የባለአደራ አስተዳደሩ ጸጥታናሰላም ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾመዋል፡፡ በጦርነቱ የመከላከያ አጋር የሆነው ታጣቂ ቡድን የሚመሩት ጀነራል ወዲ አንጥሩ፣የትግራይን ጸጥታ ኃይል እንደገና የማደራጀት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል፡፡

ባለአደራ አስተዳደሩ የፈረሱ የመንግሥት መዋቅሮችን መልሶ በመዘርጋት ሕዝቡ የመደበኛ አገልግሎት ተጠቃሚየሚሆንበትን ሁኔታ ይፈጥራል ተብሏል፡፡ አስተዳደሩ ከፌዴራል የመከላከያ፣ የፖሊስና የደኅንነት ተቋማት እንዲሁምከትግራይ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ከክልል እስከ ቀበሌ ባለው መዋቅር ውስጥ የተረጋጋ ሁኔታ እንዲፈጠር ኃላፊነትተሰጥቶታል፡፡

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *