የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርና ሎጅስቲክ አገልግሎት የየመኑ የሁቲ ታጣቂዎች በባብ-ኤል መንደብ ላይ የደቀኑትን አደጋበቅርበት እየገመገመ መሆኑ ሆርን ፍሪኩዌን ሰምቷል።
የባብ-ኤል መንደብ የመዘጋት ስጋት በኢትዮጵያ በኩል እንዴት ይታያል የሚለውን ከባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ጠይቀናል። አንድ የተቋሙ ከፍተኛ የመርከቦች እንቅስቃሴ ክትትል ባለሙያ፣ ጉዳዩ በልዩ ትኩረት እየታየመሆኑን ጠቁመዋል።
ባብ-ኤል መንደብ ለኢትዮጵያ ከሆርሙዝ በላይ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያው፣ የመዘጋቱን አደጋ “በእኛበጉሮሮ ላይ እንደመቆሞ ነው” ሲሉ ገልጸውታል። የሁቲ እንቅስቃሴ አዝማሚያ እና አጠቃላይ የግጭቱ ሁናቴ ወዴትያመራል የሚለውን ተቋሙ በየቀኑ በትኩረት እየገመገመ መሆኑ ተገልጿል።
የባብ-ኤል መንደብ መዘጋት የዓለም ንግድ ስርዓትን የሚያናጋ አደጋ መሆኑን የጠቆሙት ባለሙያው፣ ሌሎች ሀገራትምጉዳዩን በአንክሮት እንደሚከታተሉት ገልጸዋል። በእርግጥም ከሳዑዲ መርከቦች እንቅስቃሴ ገደብ አልፎ ሙሉ በሙሉከተዘጋ፣ ዓለም እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ጠቁመዋል።
ከሳዑዲ አረቢያ ጋር መጠነ ሰፊ ግጭት ውስጥ የገቡት የሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር ከፍተኛ መተላለፊያ የሆነውን የባብ-ኤል መንደብን ጨምሮ የየመን አዋሳኝ የቀይ ባህር ጠረፎችን ተቆጣጥሯል። የኢትዮጵያ 90 በመቶ ወጪና ገቢንግድ የሚጓጓዝበት፣ እንዲሁም የዓለም የባህር ንግድ መስመር ባብ-ኤል መንደብ በሁቲ እጅ ገብቷል።
በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት የሁቲ ታጣቂዎች ለጊዜው በወሳኙ የባህር መስመር በባ-ኤል መንደብ ላይ የጣሉት ገደብበሳዑዲ መርከቦች ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም፣ እንደ ሆሮሙዝ እንዳይዘጋ ስጋት ፈጥሯል።
ከሰሞኑ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ባብ ኤል መንደብን ጨምሮ በቀይ ባህር ላይ የሚገኙ ደሴቶችንም መቆጣጠራቸው ተሰምቷል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ኤርትራ እና የመን ለረጅም ጊዜያት በይገባኛል ሲወዛገቡባት የነበረቸውን ሀኒሽ ደሴትንም መቆጣጠራቸው ተሰምቷል።












