አዲስ አበባ- በሐዋሳ ከተማ የሚገኙ የሲዳማ ባንክ ሰራተኞች፣ ተቋሙ ለከተማው የሐይቅ ዳር ኮሪደር ልማት ፕሮጀክትያበረከተውን የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለመሸፈን በሚል፣ ያለሰራተኞቹ ፈቃድና ቅድመ ውይይት የአንድ ወር ሙሉደመወዛቸውን እንዲቆረጥ የወሰኑበት ቅጽ በግድ እንዲፈርሙ እየተገደዱ መሆኑን ተናገሩ።
ሰራተኞቹ ለዝግጅት ክፍላችን እንደተናገሩት የአንድ ወር ደሞዛቸው በ24 ወራት ተከፍሎ የሚያልቅ የሚጠይቅ ቅጽ በግድእንዲፈርሙ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን በምሬት አስታውቀዋል። ከባንኩ ሰራተኞች የተገኙ መረጃዎችእንደሚያመለክቱት፣ ባንኩ በቅርቡ ለሐዋሳ ሐይቅ ዳር ልማት ፕሮጀክት የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን በይፋዊማሕበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ይፋ አድርጓል። ተያይዞም የተደረገው ድጋፍ በሲዳማ ባንክ ሰራተኞች ስም የተፈጸመ መሆኑየተገለጸ ሲሆን፣ ከአስተዳደሩ የወረደው መመሪያ እያንዳንዱ ሰራተኛ የአንድ ወር ሙሉ ደመወዙን እንዲያዋጣና ይህም ለ24 ወራት እየተቀነሰ ለፕሮጀክቱ ገቢ እንዲሆን የሚያስገድድ ነው።
ይህንን ውሳኔ ተከትሎ በባንኩ የሐዋሳ ቅርንጫፍ እንዲሁም በወልደአማኑኤል ዱባለ፣ ታቦር እና ጢልቴ ቅርንጫፎችየሚሰሩ በርካታ ሰራተኞች ያለእኛ ፈቃድና ውይይት የተወሰነ መዋጮ አንፈርምም በማለት ተቃውሟቸውንአሰምተዋል። ይሁን እንጂ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ከባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ሰራተኞችን አስማምታችሁ አስፈርሙየሚል ጥብቅ ትዕዛዝ ስለደረሳቸው፣ በስራቸው ባሉ የሒሳብ ባለሞያዎች እና ኦዲተሮች ላይ ጫና በመፍጠር ሰራተኛውበግድ እንዲፈርም እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።
አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ የባንኩ ሰራተኛ ሁኔታውን ሲያስረዳ፣ ደመወዛችን በአሁኑ የኑሮ ውድነት ሁኔታ ምንምየሚበቃ አይደለም። እንደጀማሪ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን (Junior CSO) ወደ እጃችን የሚገባው 12 ሺሕ 300 ብርብቻ ነው። በዚህ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለአንድ ወር ሙሉ የሚሆን ደመወዝ ለኮሪደር ልማት ይቆረጣል ሲባል በጣም ከባድነው። ካልፈረማችሁ ከእንጀራችሁ ትፈናቀላላችሁ፣ ትባረራላችሁ የሚል ስውር ማስፈራሪያ ስላለ በጥንቃቄ መብታችንንየሚጠይቅልን አካል እንፈልጋለን” ብሏል።
ሰራተኞቹ እንደሚሉት ከሆነ፣ ከዚህ ቀደምም የሰራተኞች ብድርና ቁጠባ ተቋም በሚል ስም በተመሳሳይ ሁኔታ ያለሙሉፈቃዳቸው በየወሩ ከደመወዛቸው ከ300 ብር በላይ እንዲቆረጥ የተደረገ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ የባለቤትነት ማረጋገጫወይም የደብተር ምስክር ወረቀት እንዳልተሰጣቸውም ጨምረው ገልጸዋል። አሁን ደግሞ በድጋሚ ለኮሪደር ልማት በሚልመዋጮ መታዘዙ ሕግ ባለበት አገር እና ሁኔታ የአሰሪና ሰራተኛ ሕግን የጣሰ ነው ሲሉ ያማርራሉ።
ከደመወዝ ቅነሳው በተጨማሪ፣ ሰራተኞቹ በሲዳማ ባንክ ውስጥ ስር የሰደደ የአሰራር ችግር መኖሩን ይገልጻሉ። በሌሎችባንኮች በየዓመቱ የደመወዝ እርከን ጭማሪ (increment) የሚደረግ ቢሆንም፣ በሲዳማ ባንክ ግን ለሁለት ዓመት የሰራሰራተኛና ትናንት የተቀጠረ አዲስ ሰራተኛ ዕኩል ደመወዝ እንደሚከፈላቸው ታውቋል።
ይህ ዓይነቱ አሰራር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕግ የሚታወቅና የተፈቀደ መሆን አለመሆኑ እንዲመረመርላቸውምሰራተኞቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ሲዳማ ባንክ ሙሉ በሙሉ ወደ ንግድ ባንክነት ከመሸጋገሩ በፊት የሲዳማ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም (Sidama Microfinance / SFPI) በመባል ለረዥም ዓመታት በሲዳማ ክልልና በደቡብ አካባቢዎች ሰፊ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎትሲሰጥ የቆየ ታዋቂ ተቋም ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ወደ ባንክ ማደግ የሚችሉበትንመመሪያ ካወጣ በኋላ፣ ተቋሙ አስፈላጊውን መተማመኛ ካፒታልና መስፈርቶች አሟልቶ በ2014 ዓ.ም. በይፋ ወደ ንግድባንክነት ተሸጋግሮ ስራ ጀምሯል።











