Home / ዜና / ከደንበኞች ነዳጅ የሚቀሽቡ ማደያዎች ታገዱ

ከደንበኞች ነዳጅ የሚቀሽቡ ማደያዎች ታገዱ

የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ባደረገው የነዳጅ መቅጃ መሳሪያ ፍተሻ፣ በርካታ ማደያዎች በቅሸባ ደንበኞችን ሲያጨረበሩእንደነበር አረጋግጧል።

ባለስልጣኑ በተለያዩ ከተሞች በነዳጅ ማደያዎች የመቅጃ ማሽን (ዲስፔንሰር) ላይ ምርመራ በማድረግ እርምጃ መውሰድመጀመሩን አስታውቋል። በምርመራው ነዳጅ መቅጃ ማሽኖቻቸው ትክክለኛውን ልኬት የማያሳዩና የነዳጅ ቅሸባየሚፈጸምባቸው መሆኑን የተረጋገጡ ማደያዎች እግድ እየተጣለባቸው ነው። 

12 ማደያዎች ከሰኔ 23/2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደ ጥፋታቸው መጠን ከአንድ ወር እስከ ሁለት ወር የነዳጅ ጭነት ዕገዳተጥሎባቸዋል። በተመሳሳይ የምርመራ ሪፖርታቸው እየተዘጋጀ ባሉ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ማደያዎችም ቅጣትይጠብቃቸዋል ተብሏል።

እገዳ ከተጣለባቸው ማደያዎች መካከል ሁለት የኖክ እና ሁለት አልፋ ማደያዎች ይገኙበታል። የነዳጅ ቅሸባ ውሰጥተሳትፈው የተገኙት ማደያዎች በብዛት ኦሮሚያ እና አፋር ክልሎች፣ እንዲሁም አዲስ አበባ ውሰጥ የሚገኙ መሆናቸውሆርን ፎሪኩዌንሲ የተመለከተው የእግድ ማስተላለፊያ ደብዳቤ ያመላክታል።

ማደያዎች በመቅጃ መሳሪያ አማካኝነት ከደንበኞች ነዳጅ እንደሚቀሽቡ አሽከርካሪዎች ደርሰውበት አቤቱታ እያሰሙ ነበር።በበርካታ ማደያዎች ላይ እየታየ ነው በተባለው በዚህ የማጭበርበር ድርጊት፣ በአንድ ሊትር 200 ሚ.ሊትር ድረስእንደሚቀሸብባቸው አሽከርካሪዎች ጠቁመዋል።

ባለስልጣኑ ለነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ አቅርቦት ትስስር ፈቃድ ሲሰጥ ኅብረተሰቡን በታማኝነትና ፍትሃዊነት እንዲያገለግሉመሆኑ ይታወቃል ነገር ግን አንዳንድ ማደያዎች የፈቃድ ግዴታቸውን ቸል በማለት ተገቢ ባለሆነ ድርጊት፣ ያልተገባ ትርፍ ለማግኘት እና በተሳሳተ ልኬት ተገልጋዩን በሚጎዳ መልኩ አገልግሎት ሲሰጡ እንደሚስተዋሉ ተረጋግጧል፡፡ በቀጣይቁጥጥሩ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ከመቀሸብ ድርጊታቸው በማይታቀቡት ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃእንደሚወስድ ባለሥልጣኑ አስጠንቅቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *