አንዳንድ አዳዲስ መጻሕፍት ከታተሙ በኋላ ለገበያ እንዳይቀርቡ እና እንዳይሰራጩ እንዲሁም በአደባባይ እንዳይመረቁከፍተኛ ክትትል እያደረገ እና ክልከላም እያደረገ መሆኑን ሆርን ፎሪኩዌንሲ ሰምቷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግሥት አዲስ በሚታተሙ መጽሐፍት ላይ የይዘት ሳንሱር እያደረገ መሆኑ ታውቋል። በዚህም አዲስየታተሙ መጻሕፍ ስርጭት እንዲገደብና በአደባባይ እንዳይመረቁ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ገደብ እየጣሉ ነው ተብሏል።
በቅርቡ ለህትመት ከበቁና በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተነባቢነት ካተረፉ መጽሐፍ መካከል፣ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሦስት ሺህ ዘመናት የታሪክ ጉዞ” የተሰኘው መጽሐፍ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከገበያ ላይእንዲሰበሰብ መደረጉን የዝግጅት ክፍላችን አረጋግጧል። በቀሲስ መንግሥቱ ጎበዜ (ዶ/ር) የተጻፈው መጽሐፉ፣ ከዋናአከፋፋዩ አርጋኖን መጽሐፍ መደብር በጸጥታ አካላት መውሰዱን ዝግጅት ክፍላችን ሰምቷል። መጽሐፉ በመንግሥትየጸጥታ ኃይሎች ሲወሰድ፣ የመደብሩ ሠራተኞችም ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በሚል መታሰራቸው ታውቋል።
መጽሐፉ ከሌሎች የመሸጫ መደብሮችም በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየተሰበሰበ ነው ተብሏል። እንዲሁም ወደ ገበያያልወጣ የመጽሐፉ ቅጅ ከተቀመጠበት መጋዘን በፖሊስ ተጭኖ መወሰዱ ታውቋል።
በቅርቡ የወጣቱ ደራሲ ሰለሞን ሳህለ “ፍቅር እኮ ነው” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ የምርቃት ፕሮግራም ተዘጋጅቶ እና ቀን ተቆርጦ አንድ ቀን ሲቀረው መሰረዙ ይታወሳል። የመጽሐፉ ምርቃት የተሰረዘው፣ የመንግሥት አካላት በጣሉት ክልከላመሆኑን ደራሲው አረጋግጧል።
የምርቃት ፕሮግራሙ መሠረዝ፣ ከመጽሐፉ ይዘት ጋር የተገናኘ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን፤ የመንግሥት አካላት ከቅርብ ጊዜወዲህ አዲስ በሚታተሙ መጽሐፍ ላይ ሳንሱር መጀመራቸው ተገልጿል።
በበርካታ ተግዳሮቶች እና ጫናዎች ውስጥ የሚያልፈው የመጽሐፍት ህትመት ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለይም ደግሞ በወረቀት ዋጋ መጨመር እና ተያይዞ በህትመት ዋጋ ላይ ያለው መናር የሚይናገዳግደው ቢሆንም የዚህን አይነት እና መሰል መንግስታዊ ጫናዎች ሲታከልበት ችግሩን እንዳያባብሰው ተፈርቷል።
ከሰባት ዓመታት በፊት “የተጠለፈው ትግል” በሚል በ2011 በመድኅን ሲራጅ ተጽፎ ለንባብ የበቃው መጽሐፍ ለአንባቢ ሙሉ በሙሉ ሳይደርስ መሰብሰቡ እና ደራሲውም ከፍተኛ እንግልት እንደደረሰበት የሚታወስ ነው።












