Home / ዜና / በ34 ዓመታት ውስጥ 1050 ጋዜጠኞች ተገድለዋል

በ34 ዓመታት ውስጥ 1050 ጋዜጠኞች ተገድለዋል

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ሲፒጄ ከተቋቋመበት እና በዓለም ዙሪያ በጋዜጠኞች ላይ የሚደረሰውን በደል መመዝገብ ከጀመረበት የፈረንጆች 1992 ጀምሮ 1050 የሚሆኑ ጋዜጠኞች በዓለም ዙሪያ መገደላቸውን ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ እንዳስታወቀው ለህልፈት ከተዳረጉ ጋዜጠኞች ውስጥ ብዙ እጁን የሚይዙት ለአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን የሚሰሩ እና ሙሰና፣ ፖለቲካ እና ከጦርነት ጋር የተያያዙ ዘገባዎችን ይሰሩ የነበሩ ጋዜጠኞች ናቸው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከተፈጸሙት ግድያዎች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ፍትህ ያልተገኘባቸው ወይም አጥቂዎች ቅጣታቸውን ያልተቀበሉባቸው እንደሆነም አስታውቋል።

በዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን በጋዜጠኞች ላይ ጥቃት ሰንዝረው አጥፊዎች ተጠያቂ የማይሆኑበት አሰራር እንዲቆም የሚጠይቀው እንቅስቃሴ International Day to End Impunity for Crimes Against Journalists በተከበረበት ወቅት ሲፒጄ አጥፊዎች ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቋል።

በኢትዮጵያ ከ2018 ወዲህ ሁለት ጋዜጠኞች ለህልፈት መዳረጋቸው የተመዘገበ ሲሆን በርካቶች ደግሞ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስር፣ ለስደት እና የጋዜጠኝነት ስራ እስከማቆም የደረሱ ጋዜጠኞች መኖራቸው ይታወቃል። በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ 5 ጋዜጠኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ ለዓመታት በእስር ላይ እንደሚገኙ የሚታወስ ነው። የሚዲያ ምህዳሩን በሚመለከት በርካታ ተግዳሮቶች የተመዘገቡበት ነባራዊ ሃቅ መሆኑን በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት እየመዘገቡት ሲሆን፤ በትናንትናው ዕለት ለሰላሳ ዓመታት በስራ ላይ የቆየው እና በግል የሚዲያው ዘርፍ ፈር ቀዳጅ የነበረው ሪፖርተር ጋዜጣ መጽሔት እና የዲጂታል አማራጮች ላልተወሰነ ጊዜ በመንግስት ታግዷል።

Tagged:

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *