ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ አካባቢ የተጠለሉ ወገኖችትላንት ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም በተፈጸመባቸው የድሮን ጥቃት በርካቶች ሞተው የተረፉት ካምፑን ጥለውመውጣታቸው ለሆርን ፍሪኩዌሲ ተናግረዋል።
በተፈናቃዮች ካምፕ ላይ በተፈጸመው የድሮን ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ20 ሲሻገር፣ ተፈናቃዮች ከወደመው ካምፕወጥተው ተበታትነዋል ተብሏል፡፡
ከወለጋ ተፈናቅለው አምስት ዓመታት እና ከዛ በላይ ገደማ ሐይቅ አካባቢ በሚገኝ ጃሪ ሁለት መጠለያ ጣቢያ በተጠለሉተፈናቃዮች ላይ በተከታታይ አምስት ጊዜ በተፈጸመው የድሮን ጥቃት የሞቱ ሰዎች 23 መድረሱን የሆርን ፍሪኩዌንሲምንጮች ገልጸዋል፡፡ በጥቃቱ ክፋኛ የቆሰሉ ሰዎች ብዛት ደግሞ 40 ገደማ መድረሱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
መጠያ ካምፑ በተከታታይ በተፈጸመበት የድሮን ድብደባ እና በቃጠሎ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ስለወደመ፣ ተፈናቃዮችመጠለያ በማጣታቸው ዳግመኛ መፈናቀላቸውን ተናግረዋል። ከካምፑ ወጥተው የተበታተኑ ወገኖች የተወሰኑት በዚያውአካባቢ በየመንደሩ የተጠለሉ ሲሆን፣ ወደ ሐይቅና ደሴ ከተሞች የሄዱ መኖራቸውም ተጠቁሟል።
ተፈናቃዮች የተፈጸመባቸውን የድሮን ጥቃት ሁኔታ ሲገልጹ፣ “ሞትን ሸሽተን ሞት ተከተለን” በማለት በምሬት ተናግረዋል።በማንነታቸው ተጠቅተው ከተፈናቀሉ በኋላ “በሀገራችን ሀገር እንደሌለው ተረስትን በችግርና ትካዜ እየኖርን ነበር” የሚሉትተፈናቃዮች፣ ሞትን ሸሽተው በተጠለሉበት የተፈጸመባቸውን ጥቃት ዘርን የማጥፋት አደርገው እንደሚመለከቱትገልጸዋል።
ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ሳያንስ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ተከልክለው በችግር ውስጥ እየኖሩ እንደነበርም ገልጸዋል።ግብረሰናይ ድርጅቶች የሚሰጡት እርዳታ በመቋረጡ ለከፋ ችግር ቢጋለጡም በአንዳንድ በጎ አድረጊዎችና በአካባቢውማኅበረሰብ እገዛ መቆየታቸውንም ገልጸዋል።
የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው በካምፑ የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በሰብዓዊ ድጋፍ እጥረት ለከፍተኛ ችግር በተጋለጡበት ወቅትነው። የድሮን ጥቃት ሰለባ የሆኑት ተፈናቃዮች ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው አማራ ክልል በተያዩ አካባቢዎች ከተጠለሉ 50 ሺህ በላይ ወገኖች መካከል፣ ቱርክ ካምፕ የነበሩት 2 ሺህ ገደማ ናቸው።












