Home / ዜና / ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ካቢኔ እያደራጁ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ካቢኔ እያደራጁ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባልተለመደ ሁኔታ ከሦስት ሳምንታት በላይ ከአደባባይ እይታ ተሰውረዋል። የጠቅላይሚኒስትሩ ከአደባባይ እይታ መሰወር የተለያዩ መላ ምቶችን በማኅበራዊ ሚዲያ እያስተናገደ ይገኛል።

ሆርን ፍሪኩዌንሲ ጠቅላይ ሚነስትሩ የት ገቡ? ሲል ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ምንጮች አነጋግሯል። ለጠቅላይ ሚኒስትሩእና ለቤተ መንግስት ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት ከሆነ፣ አብይ በመጪው መስከረም ስለሚመሰርቱት አዲስመንግሥት የሥልጣን ድልድል እየሰሩ ነው ሲሉ ተናግረዋል። አብይ ጥቂት እና ቁልፍ አማካሪዎቻቸውን ይዘው በተከታታይ ሳምንታት የአዲሱን መንግሥት የሥልጣን ድልድል እያደራጁ መሆኑን ምንጮች አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቁልፍ አማካሪና ረዳቶቻቸው ጋር ስለ መስከረሙ ሹም ሽር በጥልቀት እያቀዱ ነው መባሉን ተከትሎም መረጃዎች ለዝግጅት ክፍላችን ደርሰዋል። በዚህም መሰረት በልዩ ትኩረት እየተዘጋጀ የሚገኘው ሹም ሽር፣ ጠቅላይሚኒስትሩ ራሳቸው ባዘጋጁት መስፈርት የሚመራ ነው ተብሏል። አንዱ መስፈርት አሁን በስራ ላይ ያለው ካቢኔ እያንዳንዱ አባል በተቀመጡ መስፈርቶች ተገምግሞ፣ በሥልጣን የመቀጠል አለመቀጠሉ ጉዳይ የሚወሰንበት መሆኑ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ካቢኔያቸውን  ባስቀመጡት መስፈርት መዝነው እንደሚያሰናብቱ ተጠቁሟል። በተጨማሪም ከካቢኔየሚሰናበቱት ሚኒስትሮች በአምባሳደርነት የመሾም ዕድል ያላቸው እንደሚኖሩ ምንጮች ተናግረዋል።

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በግምገማው መሠረት በምንም አይነት መንግሥታዊ ኃላፊነት የማይመደቡም ወይም በመንግስት የኃላፊነት ስፍራ ላይ የማይቀጥሉ ሊኖሩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል። በተለይም አንዱ የግምገማ መስፈርት ነው ከተባለውሙስና ጋር የተያያዘ ችግር የተገኘባቸው ባለሥልጣናት ሙሉ በሙሉ ከስራ እና ኃላፊነት ሊሰናበቱ እንደሚችሉ ተገልጿል።

በሚሰናበቱ ባለሥልጣናት ምትክ የሚሾሙ ሰዎችም እየተመለመሉ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል። በምልመላው ውስጥየገዥውን ብልጽግና የአመራር እና የአስተዳደር አቅጣጫ የሚከተሉ ሰዎች እየታጩ ነው ተብሏል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም ምንም አይነት መንግስታዊ እና ህዝባዊ ኃላፊነቶች እንዲሁም አገልግሎቶች ላይ ተሳትፎ ያልነበራቸው የማህበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች መንገዶች ተጽእኖ ፈጣሪዎችም የሹመቱ ተቋዳሽ እንዲሆኑ ሽማግሌዎችን እየላኩ መሆኑንም ዝግጅት ክፍላችን ሰምቷል። ይህን አይነት አሰራር በተለይም በጠቅላይ ሚንስትር አቢይ ካቢኔ እና የአምባሳደርነት ሹመት ውስጥ በግልጽ እንደሚስተዋል በመጻህፍት ሳይቀር ተጽፎ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በምልመላ ሂደቱ ውስጥ የብልጽግና ዋና ጽ/ቤት አመራሮች እየተሳተፉ መሆኑን ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል። ለብልፅግናታማኝነት አላቸው ተብለው የሚታሰቡ ሰዎች እየታጩ ሲሆን፣ ለተፎካካሪ ፓርቲዎችም የተወሰኑ የኃላፊነት ስፍራዎችተይዞላቸዋል ተብሏል። ነባራዊ ሁኔታው ይህን ያሳይ እንጂ በመጀመሪያዎቹ የስልጣን ዘመናቸው ጠ/ሚሩ በኮታ እና በተዋጽኦ ሳይሆን በብቃት እና በትምህርት ዝግጅት ካቢኔያቸውን እንደሚያደራጁ አስታውቀው እንደነበር አይዘነጋም።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አዲስ መንግሥት ሹም ሽር ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል። መሠረታዊ የሥልጣን ሹም ሽርናሽግሽጎች በሚጠበቅበት የመስከረም መንግሥት ምስረታ፤ ገዥው ብልጽግና የወደፊት ጥንካሬና ድክመት የሚለካበትሊሆን እንደሚችል ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል።

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *