በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተፈራ ደምሴ በታጣቂዎች ተገደሉ ።
ዋና አስተዳዳሪው የተገደሉት ነሐሴ 17/2018 አመሻሽ ላይ በተፈጸመባቸው ጥቃት መሆኑን ሆርን ፍሪኩዌንሲ አካባቢው ምንጮች ሰምቷል። ተፈራ መንገድ ላይ በነበሩበት ወቅት ደፈጣ በጣሉ ታጣቂዎች በጥይት ተመተው ክፉኛ ከቆሰሉ በኋላ ለህልፈት መዳረጋቸው ተጠቁሟል።
ዋና አስተዳዳሪው የተገደሉት ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው፣ ወይም በመንግሥት አጠራር “ኦነግ-ሸኔ” ተብሎ በሚታወቀው ታጣቂ ቡድን ሳይሆን እንዳልቀረ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ታጣቂ ቡድኑ ግድያውን እንደፈጸመው መረጃ መሠራጨቱን የአካባቢው ምንጮች ም ጨምረው ተናግረዋል።
በታጣቂዎቹ ጥቃት ከዋና አስተዳዳሪው ውጪ በሌሎች ሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። የዋና አስተዳደሩ ግድያ በአካባቢው ድንጋጤ መፍጠሩ የተጠቆመ ሲሆን፣ በወረዳው የተሰማራው መከላከያ ሠራዊት ተጣቂዎችን ለማደን መንቀሳቀሱ ተገልጿል።
ስለ አመራሩ ግድያ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ በመንግሥትም ይሁን ጥቃቱ በፈጸመው ታጣቂ ኃይል በኩል የተባለ ነገር የለም።
በሸዋ ቀጠና በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀስው የታጣቂ ቡድን፣ በተደጋጋሚ አመረሮች ላይ ግድያ መፈጸሙ ይታወሳል።
በደራ ወረዳም እስከ ወረዳው መቀመጫ ከተማ ጉንደ መስቀል ድረስ ዘልቀው በመግባት በተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጽሙ ቆይተዋል ተብሏል።












