Home / ፖለቲካ / የሱዳን ጦር የኩርሙክን አካባቢ በመቆጣጠሩ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውጥረት ተፈጥሯል

የሱዳን ጦር የኩርሙክን አካባቢ በመቆጣጠሩ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውጥረት ተፈጥሯል

ከአሶሳ ኩርሙክ ትራንስፖርት ተቋረጧል

የሱዳን ጦር ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ስትራቴጂ ከተማ ኩሙርክን በዛሬው ዕለት መቆጣጠሩተሰምቷል።

ጦሩ አንድ ሳምንት ገደማ የዘለቀ ውጊያ አድርጎ አካባቢውን መቆጣጠሩን አስታውቋል።

የሱዳን ጦር በብሉ ናይል ግዛት የምትገኘውን ኩርሙክ ከተማን እንደገና የተቆጣጠረው፣ ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች(RSF) እና ከሱዳን ሕዝባዊ ነፃነት ንቅናቄ–ሰሜን (SPLM-N) ጥምረት ጋር ከተደረጉ ውጊያዎች በኋላ ነው።

የጀነራል አል ቡርሃን ጦር የድንበር ገዢ ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ ተቀናቃኞቹ ወደ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ድንበርአፈግፍገዋል ተብሏል።

የውጊያ ግንባሩ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ይበልጥ መቅረቡን ተከትሎ፣ በአካባቢው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መቆሙን የሆርንፍሪኩዌንሲ ምንጮች ገልጸዋል። ሐምሌ 1/2018 ከሰዓት በኋላ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መቀመጫ አሶሳ ከተማ ወደኩሙርኩ ወረዳ የሚደረግ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቆም ተደርጓል።

የድንበር ላይ ውጊያው መበርታቱን ተከትሎ፣ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በነዋሪዎች ዘንድ ስጋት ተፈጥሯል። በተለይምየተፋላሚ ኃይሎች ውጊያ ይበልጥ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ኩርሙክ እየቀረበ በመጣ ቁጥር፣ ነዋሪዎች የድሮንና ከባድ መሳሪያሰለባ እንዳይሆኑ ሰግተዋል።

የሱዳኑ ጦርነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከኢትዮጵያ ድንበር ደህንነት ጋር እየተቆራኘ የመጣበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ፈጥኖ ደራሽኃይሉ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በድንበር አካባቢ ከመንቀሳቀሱ ጋር በተያያዘ፣ ከሱዳን በኩል የድሮን ጥቃት ተፈጽሞሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።

እንዲሁም ህወሓት ታጣቂዎች ከሱዳን ጦር ጋር በመሰለፍ፣ በኩሙርኩ በኩል በሚካሄደው ውጊያ ተሳታፊ መሆናቸውንየሚያመላክቱ መረጃዎች አሉ። በአልቡሃን ጦር እየተደገፈ ሱዳን ውስጥ የተደራጀው የህወሓቱ አርሚ 70 ታጣቂ ቡድን፣በኩሙርክ ግንባር መገኘት ውጥረቱን ከፍ አድርጎታል።

በአሁኑ ወቅት በህወሓት እና ፌደራል መንግሥት መካከል የተፈጠረው ውጥረት፣ ከሱዳኑ ጦርነት ጋር እየቆራኘ ነው።ህወሓት ለሱዳን ጦር ተዋጊዎችን ከማሰማራት በተጨማሪ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ጥቃት የመፈጸም አዝማሚያ እያሳየመሆኑን ሌተናል ጀነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ከኤንቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *