Home / ቴክኖሎጂ / ሰው ሰራሽ አስተውሎት የደገፈው ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ጾታዊ ጥቃት

ሰው ሰራሽ አስተውሎት የደገፈው ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ጾታዊ ጥቃት

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው እና ሃይ ባይ ያጣ እስኪመስል ድረስ በአጭር ጊዜያት ስር መስደድ የጀመረው ቴክኖሎጂ መር ጾታዊ ጥቃቶች ከህግ አስከባሪው እስከ ፖሊሲ አውጪዎች ድረስ ትኩረትን ለመነፈጉ በርካታ አመክኞዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ የመጣው የቴክኖሎጂ መራቀቅቅ ደግሞ ጉዳዩን ከማባባስም ባለፈ ችግሩን ለመቀልበስ ወደ ማይቻልበት ደረጃ እያደረሰው ይገኛል፡፡ በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው ውስን የቴክኖሎጂ እውቀት፣ ግልጽ እና በጉልህ የተቀመጠ ይህን ጉዳይ የሚቆጣጠር ህግ በአገር ደረጃ አለመኖር እንዲሁም ዓለም አቀፍ የማህበራዊ ትስስር ገጾች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩ ቃላትን የሚያነብ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ያላካተቱ በመሆኑ ችግሮችን ለመቆጣጠር ረጅም ጉዞ ጠይቋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በአጭር ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ስራ መግባት እና ይህንንም ተከትሎ የረቀቀ ሀሰተኛ መረጃዎች መሰራጨት ቀድሞውንም አሳሳቢ የነበረውን ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ ጾታዊ ጥቃቶች እንዲባባሱ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ Deep fake የተሰሩ በቀላሉ ለመለየት አስቸጋሪ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በስፋት መሰራጨት እና በተለይም ደግሞ ሴቶችን ዒላማ አድርገው መሰራጨታቸው በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጫና ከባድ አድርጎታል፡፡ በዚህ ጉዳይ በሴቶች መብት ዙሪያ የሚሰሩ ሴት አንቂዎች እና የመብት ተሟጋቾች፣ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ታዳጊ ሴቶች በኝባር ቀደምትነት ተችግሩ ተጠቂ ተደርገው ቢታዩም በየትኛውም የዕድሜ ክልል እንዲሁም የኑሮ ደረጃ የምትገኝ ሴት ከዚህ ችግር እንደማታመልጥ ለዚህ ዝግጅት ያነጋገርናቸው ሰዎች ያረጋግጣሉ፡፡ ይህን አሳሳቢ ጉዳይ በሚመለከት ከፑሊዘር ሴንተር ጋር በመተባበር ያዘጋጀነው የስዕል አውደ ራዕይ ከዚህ በታች ተያይዟል እንድትከታተሉት ይሁን፡፡

https://visit.virtualartgallery.com/thehornfrequency

ጥብቅ ማሳሰቢያ፡ የስዕሎች ባለ ሙሉ መብት እና ባለቤት ሆርን ፍሪኩዌንሲ እና ፑሊዘር ሴንተር እንደሆነም ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ እነዚህን የጥበብ ውጤቶች ያለ ተቋማቱ ዕውቅና መጠቀም እና ማሰራጨት በህግ ያስጠይቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *