Home / ፖለቲካ / የትግራይ ክልልን በሚያዋስኑት የአማራ እና አፋር ድንበር አካባቢዎች ወታደራዊ እንቅስቃሴ አይሏል

የትግራይ ክልልን በሚያዋስኑት የአማራ እና አፋር ድንበር አካባቢዎች ወታደራዊ እንቅስቃሴ አይሏል



በህወሓት እና በፌደራል መንግሥት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ፣ በትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ከፍተኛወታደራዊ እንቅስቃሴዎች መስተዋላቸው ተገለጸ።

በትግራይ ክልል በኩል ካለፈው ሳምንት ወዲህ ህወሓት ታጣቂዎቹን ወደ አማራ እና አፋር አዋሳኝ አካባቢዎችማንቀሳቀሱን ሆርን ፍሪኩዌንሲ ከአካባቢው ምንጮች ሰምቷል። በተለይም በራያ በኩል መጠነ ሰፊ ወታደራዊ እንቅስቃሴመመልከታቸውን ምንጮች ጠቁመዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በአማራ እና ትግራይ አዋሳኝ ስፍራዎች በተለይም ደግሞ ከራያ አላማጣ እስከ ራያ ቆቦ ወረዳ ድረስ እንቅስቃሴዎች መታየታቸው ታውቋል። በአፋር ክልል በኩል ደግሞ እንደ ጭፍራ ባሉት ስፍራዎች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መታየቱን ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን አስታውቀዋል።

የህወሓት ታጣቂዎች ከወትሮው የተለየ እንቅስቃሴ መኖሩን ተከትሎ፣ በአዋሳኝ አካባቢ ነዋሪዎች ላይ መረበሽ ፈጥሯል።በዚህም ትግራይን በሚያዋስኑ የአፋርና አማራ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በስጋት አካባቢያቸውን በመልቀቅ እየሸሹ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል። በተለይም ደግሞ በራያ በኩል የሚገኙ ነዋሪዎች ቀድሞም የሰላም እጦት ውስጥ የሚገኙ ቢሆኑም የአሁኑ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ደግሞ ስጋታቸውን በማናሩ ቀያቸውን ለመልቀቅ መገደዳቸውን ሆርን ፍሪኩዌንሲ አረጋግጧል።

በፌደራል መንግሥት በኩልም፣ ከባድ መሳሪያዎችን ጨምሮ የተለያዩ የወታደራዊ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው ተገልጿል።የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል ጋር በሚዋሰኑ የአፋር አካባቢዎች ገዥ ወታደራዊ ቦታዎች ላይ እየሰፈረ ነውተብሏል።

በተጠቀሱት የትግራይ እና አማራ አዋሳኝ ስፍራዎች በስፋት የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ታጣቂዎች ሙሉ በሙሉ ከመንግስት ኃይሎች ጋር ውጊያ ውስጥ መሆናቸውም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አሁን ላይ በህወሓት እና በፈዴራል መንግሥት የተፈጠረው ውጥረት፣ ዳግም ጦርነት ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት ተፈጥሯል።በሁለቱም ኃይሎች በኩል የሚስተጋቡ የሚዲያ ፕሮፖጋንዳዎች እና ወታደራዊ ዝግጅቶች ስጋቱ እንዲያይል አድርጓል።

ውጥረቱን ለማርገብ እንደ አፍሪካ ኅብረት፣ አውሮፓ ኅብረትና በአዲስ አበባ የአሜሪካ አምባሳደር ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣እስከ አሁን ተጨባጭ ለውጥ አልተገኘም።

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *