በነደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የትግራይ ክልል መንግሥት የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በዛሬው ዕለት ባወጣውይፋዊ መግለጫ፣ የፌዴራል መንግሥት «አዲስ ወታደራዊ ወረራ ከፍቶብኛል» ሲል ከሰሰ።
በመግለጫው መሠረት፣ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ከወጋህታ ጀምሮ በምዕራብ ትግራይ ዞን በጠለምት አቅጣጫ አዲስወታደራዊ እንቅስቃሴና ጥቃት መጀመሩ ተገልጿል። የፕሬቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም ቢሆን በክልሉ ላይወታደራዊ ከበባና ዝግጅቶች ሲደረጉ መቆየታቸውንም መግለጫው አክሎ ጠቅሷል።
በዚህም ምክንያት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኘው የትግራይ ሕዝብ፣ የፀጥታ ኃይሎች፣ የታጠቁ አካላት፣ የሲቪልማኅበራትና የሃይማኖት ተቋማት «ሕልውናን ለማረጋገጥ» በተደረገው ጥሪ እንዲሰባሰቡና ታሪካዊ ኃላፊነታቸውንእንዲወጡ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ የክልሉ ሕዝብም ሁኔታዎችን ተከታትሎ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሲል ጥሪአቅርቧል።
በተጨማሪም የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በቀጠናው እየተከሰተ ባለው አዲስ ውጥረትና ሊከተል በሚችለው መዘዝ ላይትኩረት እንዲሰጥና አስፈላጊውን ግፊት እንዲያደርግ በነደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የትግራይ ክልል መንግሥትጥሪውን አስተላልፏል።
በጉዳዩ ዙሪያ ከፌደራል መንግስት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።
ሕወሓት በመግለጫው ይህ ይበል እንጂ የሆርን ፍሪኩዌንሲ ምንጮች እንደተናገሩት በሸረሪና እና በረክት በተባሉ የኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ስፍራዎች ከሕወሃት ወገን ጥቃት መከፈቱን ለማወቅ ተችሏል።
ከቅርብ ቀናት ወዲህ የትግራይ ክልል በሚያዋስኑት የአማራ እና አፋር ድንበር አካባባኢዎች የወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ከሕወሓትም ወገን ሆነ ከፌደራል መንግስት በኩል መኖሩን መዘገባችን ይታወሳል።












