Home / ማህበራዊ / በኢትዮጵያ የተጠለሉ 1ነጥብ 1 ሚሊዮን ስደተኞች የረሃብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል

በኢትዮጵያ የተጠለሉ 1ነጥብ 1 ሚሊዮን ስደተኞች የረሃብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል

ከተለያዩ አገራት ተሰደው በኢትዮጵያ ተጠልለው የሚገኙ ስደተኞች በከፍተኛ ሁኔታ ካጋጠመ የዓለም አቀፍ ድጋፍ መቀነስ የተነሳ ከፍተኛ የረሃብ አደጋ እንደተጋረጠባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ UNHCR እና የዓለም የምግብ ድርጅት በጋራ ባወጡት መግለጫ አስጠንቅቀዋል።

ከጎረቤት አገራት ተፈናቅለው በኢትዮጵያ የተጠለሉ የኤርትራ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ ስደተኞች ከለጋሾች የሚገኘው ሰብዓዊ ድጋፍ ገንዘብ ምንጭ መድረቁ የተገለጸ ሲሆን፤ ለስደተኞች የሚቀርበው የለጋሾች ድጋፍ መመናመኑ እና ለጋሾች እጃቸውን ካልዘረጉ ስደተኞች በሳምታት ውስጥ ለረሃብ እንደሚጋለጡ የኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስድስት ተመላሾች አገልግሎት አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት በመጋዘን የሚገኘው የምግብ እርዳታ በሳምንታት ውስጥ እንደሚያልቅ የተገለጸ ሲሆን፣ አስቸኳይ ድጋፍ ካልተገኘ ስደተኞች ረሃብ መጋለጣቸው አይቀሬ ነው ተብሏል።

በአለም አቀፍ ደረጃ የእርዳታ ለጋሾች ድጋፍ በመቀነሱ፣ ከ70 በመቶ በላይ የስደተኞች የሰብዓዊ አገልግሎት መቋረጡ ተገልጿል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ካለፈው ከሁለት ወር ወዲህ የአለም የምግብ ድርጅት ለ780,000 ስደተኞች ያቀርብ የነበረውን የምግብ እርዳታ 40 በመቶ ለማቋረጥ ተገዷል፡፡

የሰብዓዊ ድጋፍ በተቀነሰ እና ይህንንም ተከትሎ የምግብ እጥረት በተከሰተ ቁጥር ስደተኞች ራሳቸውን ለማኖር ሌሎች አማራጮችን እንዲወስዱም ሊገደዱ እንደሚችሉ ተቋማቱ በመግለጫቸው አስጠንቅቀዋል፡፡ በተለይ ከፍተኛ ስደተኞችን እያስተናገደ በሚገኘው ጋምቤላ ክልል ከእርዳታ እጥረት ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም ችግር ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን፣ በሰሞነኛው ግጭት ውስጥም የስደተኞች ጉዳይ አቀጣጣይ ምክንያት መሆኑ እየተገለጸ ነው።

በኢትዮጵያ የተጠለሉ ስደተኞችን ለቀጣይ ስድስት ወራት ለመደገፍ 90 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ስደተኞችን በማስጠለል ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች ተብሏል፡፡ ከጎሮቤት ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ኤርትራ የመጡ ስደተኞችም ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ ሪፖርቶች ያመላክታሉ።

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *