የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፤ የፌደራል እና የክልል መንግስታት ኢትዮጵያን ከጦርነትናግጭት አዙሪት የሚያወጣ ሰለማዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ በይፋ ጠየቁ
ቴድሮስ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ “ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ሰላም እንጂ ጦርነት አይደለም” በሚል መግለጫ አውጥተዋል።በመግለጫቸው የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስቱ እና የክልል መሪዎች፣ ከጥይት ይልቅ እውነተኛ የፖለቲካ መፍትሔየሚያስገኝ ንግግር እንዲስቀድሙ ጠይቀዋል።
በአማራ ክልል ለሥስት ዓመታት የዘለቀው የትጥቅ ግጭት የበርካቶችን ሕይወት አሳጥቷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣በኦሮሚያ የደም መፋሰሱ መቀጠሉን እና ትግራይም ወደ ጦርነት ልትመለስ ከቋፍ መድረሷን ገልጸዋል። እንዲሁም እንደአፋርና ቤንሻንጉል ያሉ ክልሎች ወደ ግጭት እየተሳቡ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ከጦርነት የሚያስከትለው ሞት፣ መፈናቀልና ውድመት ነው ያሉት ቴድሮስ፣ ኢትዮጵያ ከግጭት አዙሪት መውጣት ይገባታልብለዋል። ቴድሮስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሰላም ጥሪ ሲያቀርቡ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
አገራዊ ምክክር እየተካሄደ ባለበት እና በሽዎች የሚቆጠሩ ተወካዮች ከመላው ኢትዮጵያ ተሰባስበው እየመከሩ ባለበት በዚህ ወቅት የመንግስት ኃይሎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከታጣቂዎች ጋር መዋጋታቸው የአገራዊ ምክክሩን ብዙ ትችት እንዲገጥመው አድርጓል።
ዋና ዳይሬክተሩ የሰላም ጥሪ ያቀረቡት ቀደም ሲል በአማራ እና በኦሮሚያ ሲካሄደ የነበረው ጦርነተ በተጨማሪ የፌዴራልመንግስት እና ህወሓት ወደ ዳግም ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ የሚለው ስጋት ባየለበት ወቅት ነው። በአሁኑ ወቀት በሁለቱኃይሎች መካከል ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች የሚታዩ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ሸረሪና ላይአንድ ቀን መዋጋታቸው ይታወሳል።
ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች አይለው የሚገኙት በተለይም፣ ትግራይን ከአፋር እና አማራ አዋሳኝ የራያ አካባቢዎች አካባቢ መሆኑን ልብ ይሏል።












