በአፍሪቃ ግንባር ቀደም ክፍት የገበያ ማዕከል ነው የሚባልለት መርካቶ “ይፈርሳል” የሚል ወሬ በአዲስ አበባ መናፈስ ከጀመረሰነባብቷል። እንደተባለው አልቀረም፣ ባለ ታሪኩ የገበያ ማዕከል መርካቶ መፍረስ ጀምሯል።
የመርካቶ መፍረስ የመዲናዋን ነዋሪዎች፣ ነጋዴዎችንና የከተማ ፕላን ባለሙያዎችን ዘንድ መስቀለኛ ጥያቄዎችንአስነተስቷል። ለአንዳንዶች የመርካቶን መፍረስ የዘመናዊነት ጅምር ሲሉት፣ ለሌሎች ደግሞ የታሪክ መጥፋትና የኑሮመናጋት ጅምር ነው ይላሉ።
የመርካቶ ገበያ ማዕከል ጉዳይ ከህንጻ መፍረስ ወይም እንደገና ከመገንባት በላይ ስለመሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ የሚነሳውጥያቄ “የመርካቶ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዴት ይሆናል?” እንጂ፣ “መርካቶ ይፍረስ ወይስ አይፍረስ?” የሚል ብቻ አይደለም።
መርካቶ በኢትዮጵያ ታሪክ ከገበያ በላይ የሆነ ቦታ ስለመሆኑ ብዙ ተወርቶለታል፣ ተጽፎለታል፣ ብዙ ተዜሞለታል፡፡ ባለቅኔው
“አይ መርካቶ
አገር ከየጐራው ወጥቶ
አንቺን ብሎ ነቅሎ መጥቶ
ግሣንጉሡን ጓዙን ሞልቶ
ኁልቁ መሣፍርትሽ ፈልቶ
………………………”
እንዲል ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን
መርካቶን አሁን እንዴት ከዘመን ዘመን ማሸጋገርና ታሪካዊ ይዘቱን እንደያዘ ማዘመን ይቻላል? የሚለው ጥያቄ ሲነሳ፣በተለይም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዳደር የኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ ስጋቶች ይነሳሉ፡፡ የስጋቶች መንስኤ ደግሞ ታሪካዊ እና በአዲስ አበባ ከተማ በቅርስነት የተመዘገቡ ስፍራዎች ሳይቀሩ በአንድ አዳር ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረው የከተማዋ “ትናንት” ሲጠፋ መመልከት ነው። መርካቶ በዚህ ረገድ አሁን የተያዘው የመንግስት አካሄድ ከዚህ የማፍረስ ወጀብ የሚተርፍ እንደማይሆን አስቀድመው የተናገሩ እና በኋላም ላይ በስፍራው በተወጠነው ፕሮጄክት ማካኝነት ፍራቻቸው ስጋ ወደ መልበስ ያዘነበለባቸው በርካታ ሰዎች ቅሬታዎቻቸውን ሲያሰሙ እንደነበር እና አሁንም መቀጠላቸውን ልብ ይሏል።
ከአራቱም የኢትዮጵያ አቅጣጫዎች የሚመጡ ምርቶች፣ እንዲሁም ከሌሎች ዓለም አገራት የሚገቡ ዕቃዎች፣ ጅምላአከፋፋዮች፣ አነስተኛ ነጋዴዎችን በአንድ ስፍራ የሚገናኙበት ግዙፍ የኢኮኖሚ መዘውር ስፍራ ነው።
መርካቶ የንግድ ማዕከል ብቻ አይደለም፡፡ የማኅበራዊ ትስስር፣ የእድል ፍጠራ፣ የባህል መገናኛና የኢትዮጵያ የግል ዘርፍእድገት ምልክትም ነው። ዛሬ ላይ የተፈጠሩ ትላልቅ ኩባንያዎች መነሻቸው ከትንሽ እስከ ትልቅ ንግድ የሚሳለጥበት በዚሁገበያ ውስጥ ነው። ለዚህም ደግሞ በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደ ሃብት ማማ የወጡ ባለስኬት ግለሰቦች መርካቶን መነሻቸው አድርገው በመጥቀስ የመርካቶን ውለታ እና የንግድ እንቅስቃሴን በግልጽ ሲያነሱ ይስተዋላሉ።
መርካቶች እግር ጥሎት የረገጣትን ጀማሪ ነጋዴ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሀብት ቁንጮ ላይ የምታቆናጥጥ የዕድል ማማ ነችቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ተግቶ የሰራ ለውጡን በአጭር ጊዜ የሚያይባት ስፍራ መርካቶ ነው ቢባል አያከራክርም።
መርካቶ በኮሪደር ልማት ምዕራፍ
በአዲስ አበባ የተካሄደው የኮሪደር ልማት በአንድ በኩል የከተማዋን ገጽታ ሲቀይር፣ በሌላ በኩል ታሪካዊ ቦታዎች እና ነባር መኖሪያ መንደሮችን ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ማኅበራዊ ምስቅልቅ አስከትሏል። የአዲስ አበባ ገጽታ ሲቀየር ከፒያሳ እሰከካሳንችስ፣ ከአራት ኪሎ እሰከ ቀበና ታሪካዊ ሰፈሮች አንዳልነበር ሆነዋል፡፡ ነባር እድሮች ፈርሰዋል፣ ጠንካራው ጉርብትና ተበትኗል፣ የትናንት -የዛሬ እና የነገ ትስስር ዛሬ ላይ ብቻ እንዲያበቃ የተፈረደበት በሚመስል አኳኋን ነገን ሳያይ ተቀጭቷል። ከተማን ማስዋብ፣ የተሻለ እና ምቹ ከባቢን መፍጠር ሁለት ጊዜ ሊታሰብበት የሚገባ እንዳይደለ ሁሉ፤ ወደ ተግባር ሲገባ ግን ከዚህ የሚጠልቅ ማኅበራዊ መሰረት መኖሩ የማይታለፍ ነው ሲሉ የወተወቱ የመዲናዋ ነዋሪዎች፣ ተወላጆች፣ ያገባናል ባዮች እልፍ ነበሩ፣ ናቸውም። ይሁን እንጂ መንግስት ከያዘው አቋም ፈቅ ለማለት እና የነዋሪዎችን ፍላጎት ለማድመጥ የሚያባክነው አፍታ የለውም።
ዓለም አቀፍ ተቋማት እና መገናኛ ብዙኃን በጉዳዩ ላይ ሰፊ ሀተታ ከማሰማት እና ሰፊ የቤት ፈረሳውን እስከማውገዝ መድረሳቸውም ይታወሳል። ሆርን ፍሪኩዌንሲ በተለያዩ አጋጣሚዎች ያነጋገራቸው የአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት አመራሮች ደግሞ የኮሪደር ልማቱን በሚመለከት ከመደገፍ እና ከማድነቅ የተለየ ዘገባ መስራት እንደማይችሉ በሚዲያ ተቆጣጣሪው በኩል ኮስተር ያሉ ትዕዛዝ መቀበላቸውንም አልሸሸጉም። ይህን ትዕዛዝ መተላለፍ የሚያመጣው ቅጣትም ይግባኝ የሌለው ነው እንደተባሉም አክለዋል።
የኮሪደር ልማትን ለማስፈጸም ያለ እረፍት የሚተጋው አስተዳደር ቀጣይ መዳረሻ መርካቶ ሆኗል። በአዲስ አበባ ከተማአስተዳደር መርካቶ በኮሪደር ልማት እንደገና ስለማልማት ባለፉት ሁለት ዓመታት ሲታሰብብት የቆየ ጉዳይ መሆኑን ሆርንፍሪኩዌንሲ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች አረጋግጧል፡፡
ይህ የከተማ አስተዳደሩ እቅድ አሁን ላይ በመርካቶ ገበያ ማዕከል የሚገኙ የመንግሥት ንግድ ቤቶች በማፍረስ ወደ ትግበራገብቷል፡፡ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የሚያስተዳድራቸው የንግድ ሱቆች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲፈርሱ ትዕዛዝ ወርዶ፣ፈረሳው ተጀምሯል።
በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስር የሚተዳደሩ የንግድ ቤቶች ፈርሰው በምትካቸው ዘመናዊ የንግድ ሞሎች እንዲገነቡዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡ የመንግሥት የንግድ ቤቶችን በማፍረስ የሚጀመረው የመርካቶ ገበያ ማዕከል ጉዳይ በአንድ ወገንየመዘመን ተስፋ፣ በሌላ ወገን ደግሞ የሺህዎችን ኑሮ የሚያናጋ ሆኖ ብቅ ብሏል።
የመርካቶ ነጋዴዎች ስጋት!
መርካቶ በ10 ሺዎች የሚገመቱ ነጋዴዎችን የሚያስተናገድ ትልቅ የገበያ ማዕከል እንደመሆኑ መጠን፣ ይፈርሳል የሚለውመረጃ ሲሰማ ስጋት መፍጠሩ አልቀረም፡፡ መርካቶች የሚሊዮኖች የሥራ ዕድል ምንጭ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድሞተር መሆኑ የማያጠያይቅ ጉዳይ ነው፡፡
ከ50 ዓመታት በላይ በመንግስት የንግድ ቤቶች ውስጥ የሰሩ ነጋዴዎች፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቃችሁ ውጡ ተብለናልይላሉ፡፡ የነጋዴዎቹ ስጋት የመርካቶን እንደገና የመልማት ተስፋ በመቃወም ሳይሆን፣ የሚያነሱት “ወዴት እንሂድ” የሚልየሽግግር ጥያቄ ነው።
ያነጋገረናቸው ነጋዴዎች “አይደለም የምንነግድበት፣ እቃችንን እንኳን የምናስቀምጥበት ጊዜያዊ ቦታ አልተዘጋጀልንም” ይላሉ። ለብዙዎቹ ነጋዴዎች ሱቃቸው የንግድ ቦታ ብቻ አይደለም የነገ ህልማቸው መወጣጫ መሰላል እና የብዙዎችየሥራ ዕድል ምንጭ ጭምር እንጂ፡፡
ነጋዴዎች ስጋታቸውን ሲገልጹ፣ በመርካቶ ውስጥ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የተዘረጉ የንግድ ትስስሮች በቀላሉ ወደ ሌላቦታ የሚዘዋወሩ አይደሉም ይላሉ። መርካቶች ሌላ ቦታ ላይ መፍጠር በቀላሉ የሚሳካ አይደለም የሚሉት ነጋዴዎቹ፣ለአጭር ጊዜ ቢሆንም የመርካቶ ንግድ መቋረጥ የኢኮኖሚ መናጋት አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ይሰጋሉ።
የተሻለ መርካቶ ለመፍጠር
በመንግሥት በኩል መርካቶን አሁን ካለበት ሁኔታ የተሻለ የገበያ ማዕከል የማድረግ ዕቅድ እንዳለው፣ ለነጋዴዎችተነግሯቸዋል፡፡ ለዚህም የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የሚያስተዳድራቸው የንግድ ሱቆች አፍርሶ ከአንድ ዓመት ባልበለጠጊዜ ውስጥ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ህንጻዎችን ይገነባል የሚል ተስፋ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ እንደሚለው፣ ሱቆቹ ከጊዜ ብዛት የተነሳ እጅግ አርጅተዋል፣ ከዘመናዊ የንግድ ፍላጎት ጋርም አይጣጣሙም።አዲሶቹ ህንጻዎች በፍጥነት ተገንብተው ለቀድሞ ተከራዮቹ ነጋዴዎች በቅድሚያ እድል እንደሚሰጥ በቃል ደረጃተነግሯቸዋል።
መንግሥት ለመገንባት ያቀዳቸው አዲሶቹ የንግድ ሞሎች ብዙ ተጨማሪ የንግድ ቦታዎችን በመፍጠር የመርካቶንኢኮኖሚያዊ አቅም እንደሚያሳድጉ ያምናል። ነገር ግን መርካቶን መርካቶ ያሰኙ ነጋዴዎች ተመልሰው በቦታቸው ላይ ሥራእንደሚጀምሩ እርግጠኛ አይደሉም።
ህንጻ መገንባት ወይስ እምነት መገንባት?
በዓለም ብዙ ከተሞች ያሳዩት አንድ እውነት አለ። የተሳካ የከተማ ልማት የሚለካው በሚገነቡ ህንጻዎች ብዛት ብቻአይደለም፤ ይልቁኑ በቦታው ላይ ያሉ ሰዎችን ሳያገል ወደ ተሻለ ዕድል በማሸጋገር ችሎታውም ጭምር ነው።
የመርካቶ ጉዳይም በዚሁ መነጽር መታየት እንዳለበት የከተማ ልማት ባለሙያዎች ይጠቁማሉ። መንግስት የተሻለ የንግድመሰረተ ልማት ለመገንባት ፍላጎት አለኝ ሲል፣ ነጋዴዎች ደግሞ በሽግግሩ ወቅት የንግድ ህልውናቸውን እንዳያጡይፈልጋሉ።
ባለሙያዎች እንደሚሉት ሁለቱም አቋሞች የሚገናኙበት ነጥብ ሁሉን አካታች የተደራጀ የሽግግር እቅድ መንደፍ ነው፡፡ለአብነትም መርካቶ መፍረሱ ካልቀረ አስቀድሞ ጊዜያዊ የንግድ ቦታዎች ማዘጋጀት፣ ግልጽ የግንባታ የጊዜ ሰሌዳ ማቅረብእና በባለድርሻ አካላት መካከል የተሟላ መተማመን መፍጠር ወሳኝ ነው።
መርካቶ መዘመን አለባቸው የተባሉ ያረጁ ቤቶች ስብስብ ብቻ አይደለም። በየማለዳው የሚከፈቱ ሱቆች፣ በየመንገዱየሚደረጉ ድርድሮች፣ በየአዳራሹ የተገነቡ የንግድ ትስስሮችና በትውልድ የተላለፈ የሥራ ባህል ነው።
መርካቶን የማዘመን ፍላጎት የሚነቀፍ ባይሆንም፣ የልማቱ እውነተኛ ስኬት የሚለካው የቆዩ ህንጻዎችን በአዲስ ህንጻዎችመተካት ብቻ አለመሆኑን ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡ ይልቁንም መርካቶን መርካቶ ያደረገውን ታሪካዊ የንግድ ማዕከልነት፣የማኅበራዊ ትስስርና የኢኮኖሚ ዑደት ጠብቆ ማሻገር ሲቻል ነው ይላሉ።
መንግሥት የያዘው ዕቅድ መርካቶ ከታሪኩ ሳይጠል ወደ ዘመናዊነት ማሸጋገር ካልተቻለ ትልቅ ውድቀት ሊሆንእንደሚችልም ያሳስባሉ፡፡ ለዚህም ከወዲሁ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር መወያየትና ተጨባጭ መግባባት ላይ መድረስእንዲመገባ ይመክራሉ፡፡












