የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጉባኤ በከረረ ጽንፍ በያዙ የፖለቲካ፣ ብሔር እና ሃይማኖታዊ ቡድኖች እየተፈተነመሆኑን ሆርን ፍሪኩዌንሲ ባደረገው ክትትል ተረድቷል።
ሦስትኛ ሳምንቱን ያገባደደው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ፣ ኮሚሽኑ ባረቀቃቸው ስምንት መሪ አጀንዳዎች ላይ እየመከረ ነው።ዛሬ ሐሙስ ወደ ዋናው የአጀንዳ ማጠቃለያ ምዕራፍ እየገባ በሚገኘው የምክክር ጉባኤ፣ “በጋራ ጥቅም” ላይ ተመስርተውየተባደኑ አካላት እና ተወካዮች በከፍተኛ ደረጃ መፈተኑን ምንጮች ገልጸዋል።
በተለይም ደግሞ በተደራጁ እና በሌሎች ተወያዮች ጫና ለማሳደር የሚሞክሩ ሰዎች መኖራቸውን እና ይህንንም በሚመለከት ኮሚሽኑ በስነ ምግባር ጥሰት እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል በመግለጫው አስታውቋል።
በዋናነት የምክክር ጉባኤው እየፈተኑት ነው የተባሉ ቡድኞች፣ የፖለቲካ፣ ሃይማኖት፣ ክልልና የፓርቲ ጽንፍ ይዘው ጎራለይተው ወደ ምክክር አዳራሹ በገቡ አካላት ነው ተብሏል። እነዚህ በቡድን የተደራጁ አካላት በምክክር ጉባኤው እነተሳተፉየሚገኙት፣ “በጋራ ጥቅም” ላይ የተመሰረተ የማይታረቅ አቋም የተባሉ እና አመዛኙ ተወያይ ያልተስማማባቸውን ነጥቦች በማንሳት የውይይቱን መንፈስ የሚያውኩ ሆነው መቅረባቸውም ታውቋል።
በፖለቲካ ቡድን “የጋራ አቋም” አለን ያሉ አካላት፣ አስቀድመው በጋራ በወሰዷቸው ጽንፍ የወጡ አቋሞች ላይ ተመስርተውበሌሎች ተመካካሪዎች ላይ ጫና እየፈጠሩ ነው ተብሏል። እነዚህ ቡድኖች በዋናነት የአንድን የብሔር ጥቅም በማስጠበቅላይ የተመሰረተ አቋም የሚያራምዱ ሲሆን፣ በአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች እንዲሁም በአወዛጋቢ አካባቢዎች ጉዳዮችላይ ጎራ የለዩ መሆናቸውንም ምንጮች ለሆርን ፍሪኩዌንሲ ተናግረዋል። ከጅማሬውም የዚህ መድረክ ዋነኛ ዓላማው ጽንፍ የወጡ እና ሊታረቁ የማይችሉ ሃገራዊ ሃሳቦች ወደ መሃል በመምጣት መፍትሄ የሚገኝበት እንጂ አንዱ በአንዱ ላይ ጎራ ለይቶ የሚያድምበት ሊሆን እንደማይገባ ሆርን ፍሪኩዌንሲ ያነጋገራቸው ተወያዮች አስታውቀዋል።

የኃይማኖት ጉዳይን መሰረት ያደረጉ ውይይቶችን በሚመለከትም ጥቂት ቡድኖች ከውይይት እና ከምክክር መርህ በእጅጉ ባፈነገጠ መልኩ የወከሉትን ኃይማኖት ቅድሚያ በማስቀመጥ እና ለውይይትም ሆነ ለምክክር ምንም አይነት በር በማይከፍትበት መልኩ ጽንፈኝነትን እያራመዱ የሚገኝ ሲሆን አንዳንዴም በየትኛውም የምክክር ሃሳብ ላይ አንድን ኃይማኖት ቅድሚያ በማምጣት እና በዚያ መነጸር የመመልከት ዝንባሌ በመኖሩ የምክክሩን መንፈስ የሚቀይር ሆኗል ተብሏል።
በምክክር ጉባኤው ውስጥ በአብዛኞቹ አጀንዳዎች ላይ በግልጽ ገኖ የታየው ሃይማኖታዊ ቡድን፣ እንደ ሀገር ኢትዮጵያበቆመችባቸው መሰረቶች ላይ ጭምር ጥያቄ የሚያነሳ ሲሆን፣ አብዛኞቹን አጀንዳዎች በሃይማኖት አንጻር በከረረ ጽንፍይመዝናል ተብሏል። ለአብነትም ኢትዮጵያ በዓለም በልዩነት የምትታወቅበትን የራሷን የቀን አቆጣጠር ላይ ይቀየር የሚልአቋም አለው ተብሏል።
በዚህ ቡድም የተያያዘ የኢትዮጵያ ቀን አቆጣጠር የመቀየር አጀንዳ፣ አሁን ያሉ የዓመት የቀናት፣ የወራት አቆጣጠሮችተሰርዘው በአዲስ እንዲተኩ አቋም ይዟል ተብሏል። እንዲሰረዝ በሚፈልገው የኢትዮጵያ ቀን አቆጣጠር፣ የጎርጎሮሳውያኑንአቆጣጠር የመተካት አጀንዳ ይዞ መቅረቡም ተጠቁሟል።
የሃይማኖታዊ ቡድኑ ጽንፍ የወጣ አቋም ሌሎች ተመካካሪዎች ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ተብሏል። በጋራ መግባባት ላይየተመሰረተውን የምክክር መርህም ማናጋቱን ምንጮች ጠቁመዋል።
ሌላኛው ቡዱን በክልል ተወካዮች በኩል በአብዛኛዎቹ አጀንዳዎች ላይ የሚታይ የጽንፍ አቋም ነው ተብሏል። በተለያዩአጀንዳዎች ላይ የሚሳተፉ የክልል ተወካዮች ማታ ማታ ቡድን በመፍጠር፣ የመጡበትን ክልል አቋም በተመሳሳይ ሁኔታ ይዞየመቆም ሁኔታ ታይቷል።
በርከት ባሉት የክልል ቡድኖች ላይ በአካባቢዎች የወሰንና ባለቤት ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል። በተለይም እንደ አዲስ አበባ ባሉአወዛጋቢ አካባቢዎች ላይ የክልል ተወካዮች የከረረ የልዩነት አቋም ያንጸባረቁ ሲሆን፣ ቀስ በቀስ የምክክሩ ተሳታፊዎች ወደሁለት ጎራ መለየቱ ተጠቁሟል።
በአዲስ አበባ ጉዳይ አብዛኞቹ የክልል ተወካዮች የፌደራል ከተማ ወይም ራስ ገዝ ከተማ ትሁን የሚል አቋም እየያዙመጥተዋል። በአንጻሩ የኦሮሚያ ክልል ወኪሎች በኩል አዲስ አበባ ወደ ክልላችን በባለቤትነት መጠቃለል አለባት የሚልአቋም ይዘዋል ተብሏል። ይህ ጉዳይ በእርግጥም የቆየ እና በርካታ ዓመታትን ሲያወዛግብ የቆየ ዘላቂ መፍትሄም የሚያሻው ጓይ መሆኑ የታመነበት እንደሆነ ይታወቃል። ተወያዮች እንደሚሉት ግን ይህን ምክንያት በማድረግ ጫና ማሳደር እና ሌሎች ተወካዮችን አሳንሶ የመመልከት አዝማሚያ በመኖሩ እንዲያውም ከውይይቱ ራሳችንን ለማግለል በየቀኑ እየተቃረብን ነው ሲሉም ተናገርዋል።
ጉባኤ መበተን የሚያልሙ ቡድኖች
በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ዓለማ ባነገበው ምክክር፣ ጽንፍ የወጣ አቋም የያዙ ቡድኖችጉባኤ እስከመበተን የደረሰ አደጋ የደቀኑበት አዝማሚያ መኖሩን ምንጮች ጠቁመዋል።
የጽንፍ አቋም ከያዙት ቡድኖች መካከል፣ በምክክሩ ፍላጎታችን ማሳካት ከልቻልን ጉባኤውን “በትነን እንወጣለን” የሚልዝንባሌ እያሳዩ ከፍ ሲልም በሚደመጥ መልኩ እስከመናገር እየተደረሰ ነው ተብሏል። የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ተወካዮችንጨምሮ በምክክሩ ላይ እንዲህ አይነት አደጋ የደቀኑ ቡድኖች፤ በሌሎች ተመካካሪዎች ላይ የስነ ልቦና ጫና እየፈጠሩ መሆኑተጠቁሟል።
የምክክር ጉባኤውን በስኬት የመጠናቀቅ ተስፋ ላይ ስጋት የደቀኑ ቡድኖች፣ በወሳኙ ምዕራፍ ላይ እንዳይንጸባረቅከተሳታፊዎች ቅሬታ መቅረቡን ምንጮች ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ በምክክር ሂደቱ ላይ ከፍተኛ የስነ ልቦና እና ልዩ ልዩ ጫናዎችን እያስተናገዱ የሚገኙ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ምክክሩን ትተው ለመውጣት ሃሳብ እንዳላቸውም ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል።
ከጅማሬው ጀምሮ በርካታ አስተያይቶችን ሲያስተናግድ የቆየው የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን በዓመታት ሂደቶቹ ብዙ ቅሬታዎች ተሰምተውበታል። የአጀንዳ ማሰባሰቡ አልቆ ወደ ምክክር ከተገባ በኋላም የተለያዩ መረጃዎች ሲያፈነግጡ እና በተለያዩ መንገዶችም ለህዝብ ሲደርሱ ቆይተዋል። ከታጠቁ ኃይላት ጋር ወይም ተወካዮችን በምክክር ሂደቱ አለማካተታቸው የታአማኒነቱን እና ሃቀኛ አገራዊ መፍትሄ ለማምጣት አይሰራም እንዲባልም አድርጓል።
ይሁን እንጂ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በተደጋጋሚ የሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል ማካተታቸውን ሲገልጹ መቆየታቸውም ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት አገራዊ ምክክር እየተከናወነ ባለበት ወቅት በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች የተጠናከረ ውጊያ ታጣቂዎች ከመንግስት ኃይል ጋር እያደረጉም ይገኛሉ።











