በግብፅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የእስር፣ እንግልት እና ለሞት አደጋ እየተጋለጡ መሆኑን ምንጮች ለሆርንፍሪኪዌንሲ ተናገሩ። በግብፅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በተለይም ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ከባድ የእስር፣የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና እንግልት እየገጠማቸው መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
በካይሮ የሚገኙ ስደተኞች እንደሚገልጹት፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) የሚሰጣቸውን ህጋዊ የመኖሪያ እና የጥገኝነት ማመልከቻ ወረቀቶች የያዙትን ጨምሮ በግብፅ የደህንነት አካላት ተይዘውለእስር እየተዳረጉ ይገኛሉ።
ተጠያቂነት በሌላቸው ኢ-መደበኛ እስር ቤቶች ውስጥ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩት ስደተኞች፣ ለአካላዊ እና ስነ-ልቦናዊእንግልት፣ እንዲሁም ለከፋ የጤና ቀውስ እየተጋለጡ ነው።
በአስቸጋሪ ቦታዎች ረጅም ጊዜ በጨለማ ከፍል ውስጥ የሚታሰሩ ስደተኞች፣ ለሞትና ለከፋ የጤና እክል እንደሚጋለጡምንጮች ተናግረዋል። በቅርቡም ያሬድ ገረመው የተባለ ኢትዮጵያዊ በእስር ቤት ውስጥ ህይወቱ አልፎ አስከሬኑ ወደ ሀገርቤት መላኩንም ሆርን ፍሪኩዌንሲ ከምንጮቹ አረጋግጧል።
የUNHCR የአገልግሎት አሰጣጥ መዘገየት እና የሰነድ ማደሻ ሂደት ጊዜያት እርዝመት ስደተኞቹን ይበልጥ ለእስር ተጋላጭ እንዳደረጋቸው ለማወቅ ተችሏል።
በአሁኑ ወቅት በካይሮ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በነፃነት ወጥተው መስራትም ሆነ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት መጠቀም ስጋት እንደሆነባቸው የተነገረ ሲሆን፤ በተለይ በሴቶች ላይ የሚደርሰው መብት ጥሰትም የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱ ተጠቅሷል። በፖሊስ ተይዘው የሚታሰሩ ሴት ስደተኞች ለጾታዊ ጥቃት የሚጋለጡበት ሁኔታ መኖሩ ተጠቁሟል።
በካይሮ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ በፖለቲካ፣ በሃይማኖት እና በብሔር መከፋፈሉ እርስ በእርስ ለመጠባበቅና ለመደጋገፍአልተቻለም ተብሏል። ስደተኛ ዜጎች ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው በጋራ መብታቸውን የሚያስክበር ገለልተኛአደረጃጀት እንዲፈጥሩ ጥሪ ቀርቧል። ጉዳዩን በሚመለከት ከUNHCR በኩል ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። በጉዳዩ ላይ ተከታታይ ዘገባዎችን ወደ እናንተ ስለምናደርስ ከUNHCR እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመከታቸው አካላት የሚሰጥትን ምላሽ ይዘን እንቀርባለን።












