Home / ፖለቲካ / ‹‹የወልቃይት ህዝብ በፓርላማ ወኪል እንዲኖረው እየተሰራ ነው›› አሸተ ደምለው

‹‹የወልቃይት ህዝብ በፓርላማ ወኪል እንዲኖረው እየተሰራ ነው›› አሸተ ደምለው

ለበርካታ ዓመታት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የውጥረት ቀጠና የሆነው የወልቃይት እና አካባቢው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልና እንዲኖረው እየተሰራ መሆኑን የወልቃይ ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳዳሪ አሸተ ደምለው ለሆርን ፍሪኩዌንሲ አስታውቀዋል፡፡

ባለፉት አምስት የነጻነት ዓመታት የወልቃይት ሕዝብ በፓርላማ ወኪል አልነበረውም ያሉት አሸተ፣ ሰባተኛው ሃገራዊ ምርጫው በዞኑ እንዲካሄድ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። በመጨረሻም፣ በሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት መሠረት በፓርላማም ሆነ በክልል ወኪል ያለው የአመሰራረት ሥርዓት ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑን አስተዳዳሪው አመላክተዋል።

የወልቃይት ሕዝብ ትግርኛ እና ዐረብኛ ተናጋሪ መሆኑን አብራርተዋል። ቢሆንም ግን ቋንቋውን ስለተናገረ ብቻ ትግሬ ነው ወይም ሱዳን፣ ዐረብ ነው ሊያስብለው እንደማይቻልም ጠቁመዋል። “አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም” የሚል ብሂል የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ እንዳለው አሸተ ገልጸዋል።

ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ በአንድ ወቅት የአካባቢውን ሕዝብ ሲገልጹ የተወላገደ አማርኛ እና የተወላገደ ትግርኛ ይናገራል ሲሉም መደመጣቸው የሚታወስ ነው፡፡

በአካባቢው ባለው የይገባኛል ውዝግብን በሚመለከትም አስተዳዳሪው_የወልቃይት ሕዝብ ማንነትና የይገባኛል ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት እና ይህንንም በጽኑ እንደሚያምኑበት ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል፡፡

አስተዳዳሪው የሕዝቡ ዋነኛ ፍላጎት ሰላም መሆኑን ጠቁመው፣ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥያቄ አቅርበዋል። ጥያቄያቸውም “በሰላምና በሕግ እንጂ በጉልበት እንደማይፈታ” ሕዝቡ ያምናል ብለዋል። አያይዘውም ቢሆንም ግን “ህወሓት ዛሬም ለጦርነት እየተዘጋጀ ነው፤ ከስህተቱ አልተማረም” ሲሉ ሕወሓትን ከሰዋል፡፡

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *