Home / ፖለቲካ / የቁጫ ብሔረሰብ የማንነት “ድፍጠጣ” እየተደረገበት ነው ተባለ

የቁጫ ብሔረሰብ የማንነት “ድፍጠጣ” እየተደረገበት ነው ተባለ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ውስጥ የሚገኘው ቁጫ ብሔረሰብ “የወረዳ መዋቅር እንጂ የራሱ ማንነት የለውም” በሚል ጫና እየተደረገበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ቁጫ የራሱ ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋና የዘመን መለወጣ ያለው ብሔረሰብ ቢሆንም፣ በዞኑ መንግሥት “ድፍጠጣ” እየተፈጸመበት መሆኑን የብሔረሰቡ ተወካዮች ለሆርን ፍሪኩዌንሲ ገልጸዋል፡፡ የብሔረሰቡ ተወካዮች ባለፈው ሳምንት “ዎዳላ ጋዜ” የዘመን መለወጫ ማክበራቸውን ተከትሎ፣ ከዞኑ አስተዳደር ከፍተኛ ጫና እየደሰረባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቁጫ ብሔረሰብ “ዎዳላ ጋዜ” የተሰኘውን የዘመን መለወጫ እንደማንኛውም የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ማክበሩ በዞኑ አስተዳደር ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ የዞኑ አስተዳደር ቁጫ ከጋሞ የተለየ የራሱ የብሔረሰብ ዘመን መለወጫ የለውም በሚል የተቃውሞ መግለጫ አውጥቷል፡፡

የዞኑ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ “የቁጫ ሕዝብ በጋሞ ዞን ውስጥ የሚገኝ የወረዳ መዋቅር ነው” በማለት የራሱን የዘመን መለወጫ እንደሌለው ገልጿል፡፡ የቁጫ ብሔረሰብ ተወካዮችና ተወላጆች የ “ዎዳላ ጋዜ” የዘመን መለወጫቸው በአዲስ አበባ ማክበራቸው ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት “ዎዳላ ጋዜ” በመስከረም ወር ከሚከበሩ የብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓላት ብሎ በሰራው ዘገባ፣ የቁጫ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ የጋሞ ዞን አስተዳደር ያነሳውን ተቃውሞ ተቀብሎ፣ “ዎዳላ ጋዜ” የቁጫ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ተብሎ መገለጹን አስተባብሏል፡፡

የዞኑ አስተዳደር የቁጫ ብሔረሰብ የራሱ ዘመን መለወጫ የለውም በሚል የብሔረሰብ ተወካዮችን ለማሰር እየተንቀሳቀሰ መሆኑንሆርን ፍሪኩዌንሲ ባደረገው ማጣራት መረዳት ችሏል፡፡ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ በዓሉን ያከበሩ የብሔረሰቡ ተወካዮችና ታዳሚዎች ላይ ክትትል እየተደረገባቸው ነው ተብሏል፡፡

የቁጫ ብሔረሰብ የራሱ ታሪካዊ ማንነት ያለው መሆኑን መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ የአንትሮፖሎጂስቱ ሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ “የቁጫ ሕዝብ ታሪከ እስከ 2007 ዓ.ም.” በተሰኘው መጽሐፋቸው፣ “ቁጫ” የሚለው ቃል አካባቢውን፣ ሕዝቡንና ቋንቋውን የሚወከል መሆኑን ይሳረዳል፡፡

የብሔረሰቡ ተወካዮች በአሁኑ ወቅት የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የተሰኘ የፖለቲካ ፓርቲ አቋቁመው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ የብሔረሰብ ፓርቲው መሪ ረ/ፕሮፌሰር ገነነ ገደቡ በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የቁጫ ምርጫ ክልል አሸናፊ ሆነው ፓርላማ መግባታቸው ይታወሳል

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *