Home / ፖለቲካ / ኤርትራ እና ህወሓት የተባበርንበት የጦርነት ዝግጅት የለም አሉ

ኤርትራ እና ህወሓት የተባበርንበት የጦርነት ዝግጅት የለም አሉ

ከሰሞኑ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ተፈርሞ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በተላከው ደብዳቤ ክስ የቀረበባቸው የሕወሓት እና የኤርትራ መንግስት በየፊናቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በምላሻቸውም ኹለቱም ወገኖች ምንም አይነት የጦርነት ዝግጅት በበኩላቸው እንደሌለ እና አሳሳች መረጃ መሆኑን በተናጠል እና በይፋ በሰጡት ምላሽ አስታውቀዋል፡፡

ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ይዘት ባለው መግለጫቸው ኹለቱም አካላት የቀረበባቸው ክስ መሰረተ ቢስ መሆኑንም አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ክስ ምላሽ የሰጡት የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል፣ በደብዳቤው የቀረቡትን ዝርዝር ክሶች “አሳሳች” በማለት አስተባብለዋል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተፈርሞ የቀረበው ክስ “ኢትዮጵያን እንዲሁም የዓለም ሕዝብ የናቀ ነው” ሲሉ አጣጥለዋል።

የማነ “ላለፉት ኹለት ዓመታት ብልፅግና ‘ከተቻለ በሕጋዊ መንገድ ካልተቻለ በወታደራዊ ኃይል ሉዓላዊ የባህር በር ማግኘት’ የሚለውን ደጋግሞ ሲያስተጋባ ቆይቷል” ሲሉም አክለዋል። አያይዘውም “ግዛት ማስፋፋትን ዒላማ ያደረገው ይህ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በግድየለሽ እና ተንኳሽ ዛቻም የታጀበ ነው” ብለዋል።

ኤርትራ ከዚህ ቀደምም እንደገለጸችው “እንዲህ ወዳለው ነገር ተጎትታ አትገባም” ሲሉ የቀረበውን ክስ ተከላክለዋል፡፡ የማነ በቀረበው ክስ የሚመለከታቸው ያሏቸው አካላት “በዚህ ድርጊት እንዳይናወጡ” ሲሉም በስም ያልጠቀሷቸውን አካላት መክረዋል፡፡

ህወሓት በበኩሉ በሰጠው ምላሽ የቀረበበትን ክስ አስተባብሎ የፌደራል መንግሥቱን ቀጠናዊ ግጭት በመጠንሰስ ወንጅሏል። የፌደራል መንግሥት በህወሓት “ሀሰተኛ” ክስ በማቅረብ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ትኩረት ለማስቀየር እየሞከረ መሆኑ በብዳቤው ተገልጿል፡፡

የህወሓቱ ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ በጻፉት ደብዳቤ የፌደራል መንግሥቱን ወንጅለዋል፡፡ ህወሓት ለቀረበበት ምላሽ በሰጠበት ደብዳቤ የፌደራል መንግሥቱ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ከመተግበር ይልቅ፣ ዳግም ግጭት ለመቀስቀስ ሰበብ እየፈለገ ነው ብሏል፡፡

ህወሓት በቀጥታ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በላከው ደብዳቤው አፈጻጸሙ የተቋረጠው የፕሪቶሪያ ስምምነት በአስቸኳይ ተግምግሞ እንዲፈጸም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግፊት እንዲያደርግ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮብ ጢሞቲዎች ከሰሞኑ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጻፉት ድበዳቤ ኤርትራን መወጀላቸው ይታወሳል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ አህመድ አስተዳደር በቀቀረበው ክስ ኤርትራ እና ህወሓት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ “ጦርነት ለማወጅ” እየተዘጋጁ ነው በማለት ወንጅሏል፡፡

በኤርትራ ላይ የቀረበው ክስ ተደራራቢ ሲሆን፣ ከህወሓት ጋር አብሮ ጦርነት ከማወጅ በተጨማሪ በውስጥት ጉዳዮች ጣልቃ መግባትን ይጨምሯል፡፡ እንዲሁም ከሁለት ዓመት በላይ ከመንግሥት ጋር እየተዋጉ የሚገኙት የአማራ ፋኖ ኃይሎችን በመደገፍ የኤርትራ መንግሥት ተወንጅሏል፡፡

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *