Home / ፖለቲካ / የአልጀርስ ስምምነት ይሠረዝ በሚል ጥሪ የሀገር ውስጥ ዘመቻ ተጀመረ

የአልጀርስ ስምምነት ይሠረዝ በሚል ጥሪ የሀገር ውስጥ ዘመቻ ተጀመረ

ከ20 ዓመታት በፊት ከፍተኛ ደም መፋሰስ የተመዘገበበት የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት እንዲያበቃ እና በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ታስቦ ታህሳስ 3 ቀን 1993 ዓ.ም በአልጀሪያ ዋና ከተማ አልጀርስ የተፈረመው የሰላም ስምምነት እንዲሰረዝ የሚጠይቅ ዘመቻ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተቀሰቀሰ መሆኑን ሆርን ፍሪኩዮንሲ ሰምቷል።

ይህ ስምምነት በቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና በኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የድንበር ጦርነቱን ለማስቆም የተደረገ ነበር። ይሁን እንጂ ስምምነቱ ተግባራዊ ባለመሆኑ እና በተለይም በድንበር ጉዳይ ላይ በነበረው አለመግባባት ሳቢያ፣ ውሉ አሁን ላይ የሁለቱን አገራት ጥቅም በሚያሳካ መልኩ እየሰራ አይደለም የሚል አስተያየት እየሰፋ መጥቷል።

ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ካነሳችበት ጊዜ ወዲህ በሁለቱ ሃገራት መካከል የቃላት ምልልስ መጠናከሩን ተከትሎ ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሰርዛ አዲስና የቀይ ባህርን ጉዳይ ያካተተ ድርድር ልታደርግ ይገባል የሚል ዘመቻ እየተስፋፋ መምጣቱን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል፣ ኤርትራ ውሳኔው ተግባራዊ እስካልሆነ ድረስ ሰላም አይኖርም በሚል አቋም በመቆየቷ፣ ስምምነቱ ለረጅም ዓመታት ያለተግባር እንዲቆይ ምክንያት ሆኗል። በመሆኑም፣ ይህ ሰነድ ዓላማውን ባለማሳካቱና ተግባራዊነቱ ለዘለቄታው በመቆሙ ምክንያት “የሞተ ሰነድ” ተደርጎ መታየት እንዳለበት የፖለቲካ ተንታኞችም በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል።

ተንታኞች እንደሚሉት፣በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስተዳደር በሁለቱ አገራት መካከል የተጀመረው አዲስ የሰላም እና ወንድማማችነት ምዕራፍ፣ የድሮውን የአልጀርስ ስምምነት በመሰረቱ የተሻገረ ነው። በመሆኑም፣ አዲሱን ግንኙነት በሕግና በፖለቲካ ግልጽነት ለማስቀጠል ሲባል የድሮውን ውል በመሻር፣ አዲስና ሁሉን አቀፍ ድርድር የማካሄድ አስፈላጊነት ላይ ይህ ዘመቻ ትኩረት አድርጓል ነው የተባለው።

ዘመቻው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅና ታሪካዊ ይዞታዎችን ከመመለስ አንፃር የአልጀርሱን ስምምነት መሰረዝ ወሳኝ እርምጃ ነው ሲል እየገፋበት ይገኛል።

Sign Up For Daily Newsletter

Stay updated with our weekly newsletter. Subscribe now to never miss an update!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *