የአውሮፓ ኅብረት የግብፅን የቅኝ ግዛት እሳቤ ተቀብሎ ማስተጋባቱ ኢትዮጵያ እንደማትቀበል አስታውቃለች።
አውሮፓ ኅብረት ከሰሞኑ ከግብፅ ጋር ባደረገው ስብሰባ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ወገንተኛ አቋም አንጸባርቋል። ኅብረቱ በህዳሴ ግድብ ላይ በግልጽ ካይሮን ደግፎ አቋም የያዘው የአውሮፓ-ግብፅ ጉባኤ የጋራ መግለጫ ላይ ነው። ኅብረቱ የግብፅን የቅኝ ግዛት እሳቤ ተጋርቶ አቋም መያዙን በብራሰልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰጠው የመግለጫ ምላሽ ተቃውሞውን ገልጿል። ኤምባሲው በመግለጫው አውሮፓ ኅብረት ገለልተኛ ሚና መጫወት ሲገባው፣ ለግብፅ ውግንና ይዞ አቋም መውሰዱ ‘አሳዛኝ’ ነው ሲል በብርቱ ተቃውሟል።
ኢምባሲው በመግለጫው አውሮፓ ኅብረት የያዘው አቋም የኢትዮጵያን በአባይ ውሃ ላይ ያላትን ተጠቃሚነት ታሳቢ ያላደረገ ነው ብሏል። ኅብረቱ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላትን ግብፅና ጥቅምና ህልውና ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ አካሄዶች እንደማይቀበል ገልጿል።
የኢትዮጵያ ኤምባሲ በብራሰል በሰጠው ምላሽ ኅብረቱ የተናጠል አቋም ደግፎ መቆሙ አጥቦቆ ተቃውሟል። አውሮፓ ኅብረት ገለልተኛ አደራዳሪነት አቋም ይሆ በዓለም አቀፍ ሕግ አግባብ ችግሮችን ለመፍትታ መቆርቆር እንደነበረበት ተመላክቷል።
ኅብረቱ ለግብፅ ውግንና ማሳየት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ታራካዊ ግንኙነት ታሳቢ ያደረገ አለመሆኑን ኤምባሲው ገልጿል። ኢትዮጵያ በጋራ መግለጫው ላይ የታየውን ወገንተኝነት ለማረም ከኅብረቱ አባል ሀገራት ጋር ተጨባጭ ሁኔታዎች መሰረት ያደረገ ውይይት ታደርጋለች ተብሏል።
ግብፅ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረበት ጊዜ እሰከ መጠናቀቁ የዘለቀ የፖለቲካ እና ዲፕሎማሲያዊ ጫና ለመፍጠር መንቀሳቀሷን ኤምባሲው አስታውሷል። ኢትዮጵያ በሉዓላዊ ግዛቷ የመልማት መብቷ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የተፋሰሱ አገራት በአባይ ውሃ ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደምትሻ ተመላክቷል።
ግብፅ የግድቡን ግንባታ ከመጠናቀቅ ማስቀረት አለመቻሏን ተከትሎ፣ ከተመረቀ በኋላ እንደ አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰች ነው። በኢትዮጵያ በኩል በግድቡ ጉዳይ ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ሊሰጥ የሚችል አቋም እንደማይያዝ እየተገለጸ ነው።
ኢትዮጵያ ምክንያታዊ መሰረት የሌለው አስገዳጅ ስምምነት አልፈርምም በማለቷ ድርድሩ ተቋርጦ ይገኛል። የሦስትዮሽ ድርድሩ ከቆመበት ይቀጥላል የሚል ፍላጎት ከግብፅ በኩል ቢነሳም፣ በኢትዮጵያ በኩል የቅኝ ግዛት እሳቤን አልቀበልም በማለት በአቋሟ ጸንታለች።










